ኢሳይያስ 36:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ሕዝቅያስን አትስሙ፤’ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ‘ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ኑ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፥ ከጉድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 “ሕዝቅያስን አትስሙ። የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፤ ‘ከእኔ ጋራ ተስማሙ፤ ወደ እኔም ውጡ። ከዚያም እያንዳንዳችሁ ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ! የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፦ ወደ እኔ ኑና ከእኔ ጋር ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላ የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጒድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ሕዝቅያስንም አትስሙ፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ በሕይወት ልትኖሩ ብትወድዱ ሁላችሁ ወደ እኔ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ትጠጣላችሁ፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ሕዝቅያስንም አትስሙ፥ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ውጡ፥ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፥ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፥ Ver Capítulo |