Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 10:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ጽኑ​ዓን ሰዎች ሁሉ ከገ​ለ​ዐድ ተነ​ሥ​ተው የሳ​ኦ​ልን ሬሳ የል​ጆ​ቹ​ንም ሬሳ​ዎች ወሰዱ፥ ወደ ኢያ​ቢ​ስም አመ​ጡ​አ​ቸው፤ በኢ​ያ​ቢ​ስም ካለው ከት​ልቁ ዛፍ በታች አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቀበሩ፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ጀግኖቻቸው ሁሉ ተነሥተው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ወደ ኢያቢስ አመጡ፤ ዐጽማቸውንም ኢያቢስ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጽኑዓን ሰዎች ሁሉ ተነሥተው የሳኦልን ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ወሰዱ፥ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በኢያቢስም ካለው ከባሉጥ ዛፍ በታች አጥንቶቻቸውን ቀበሩ፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ኀያላን የሆኑ ሰዎች ሄደው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ በመውሰድ ወደ ያቤሽ አመጡ፤ በዚያም በወርካ ዛፍ ሥር ከቀበሩአቸው በኋላ ሰባት ቀን በሙሉ ጾሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ጽኑዓን ሰዎች ሁሉ ተነሥተው የሳኦልን ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ወሰዱ፤ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በኢያቢስም ካለው ከትልቁ ዛፍ በታች አጥንቶቻቸውን ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 10:12
10 Referencias Cruzadas  

አብ​ራ​ምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚ​ያች ምድር አለፈ፤ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በዚ​ያን ጊዜ በዚ​ያች ምድር ነበሩ።


የር​ብቃ ሞግ​ዚት ዲቦ​ራም ሞተች፤ ከቤ​ቴል በታች ባላን በሚ​ባል ዛፍ ሥርም ተቀ​በ​ረች፤ ያዕ​ቆ​ብም ስሙን “የል​ቅሶ ዛፍ” ብሎ ጠራው።


በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወዳ​ለ​ችው ወደ አጣድ አው​ድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለአ​ባ​ቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደ​ረ​ገ​ለት።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ገና ሳይ​መሽ ዳዊ​ትን እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ሊጋ​ብ​ዙት መጡ፤ ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ሳት​ጠ​ልቅ እን​ጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀ​ምስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፥ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ” ብሎ ማለ።


የገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ሁሉ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በሳ​ኦ​ልና በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን ሁሉ ሰሙ።


ከአ​ይ​ሁ​ድም ስለ ወን​ድ​ማ​ቸው ሊያ​ጽ​ና​ኑ​አ​ቸው ወደ ማር​ያ​ምና ወደ ማርታ የሄዱ ብዙ​ዎች ነበሩ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከአ​ንድ ወር በኋላ አሞ​ና​ዊው ናዖስ መጣ፤ በኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓ​ድም ሰፈረ፤ የኢ​ያ​ቢ​ስም ሰዎች ሁሉ፥ “አሞ​ና​ዊ​ውን ናዖ​ስን ቃል ኪዳን አድ​ር​ግ​ልን፤ እኛም እን​ገ​ዛ​ል​ሃ​ለን” አሉት።


የመ​ጡ​ት​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች፥ “የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓ​ድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተ​ኰሰ ጊዜ ድኅ​ነት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል በሉ​አ​ቸው” አሉ​አ​ቸው። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ቢስ ሰዎች ነገሩ፤ ደስም አላ​ቸው።


የሳ​ኦ​ል​ንም ሬሳ፥ የልጁ የዮ​ና​ታ​ን​ንም ሬሳ ከቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አወ​ረዱ፤ ወደ ኢያ​ቢ​ስም አመ​ጡ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም አቃ​ጠ​ሉ​አ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos