Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 12:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የአ​ሞ​ንም ልጆች ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣ​ባ​ችሁ ባያ​ችሁ ጊዜ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉ​ሣ​ችሁ ሳለ፦ እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን አላ​ች​ሁኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ ግን፣ ምንም እንኳ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ቢሆንም፣ ‘አይሆንም፤ የሚገዛን ንጉሥ እንፈልጋለን’ አላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ እንደመጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ ግን፥ አምላካችሁ ጌታ ንጉሣችሁ ቢሆንም እንኳን፥ ‘አይሆንም፤ የሚገዛን ንጉሥ እንፈልጋለን’ አላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ንጉሣችሁ ሆኖ ሳለ የአሞን ንጉሥ ናዖስ በእናንተ ላይ መነሣቱን ባያችሁ ጊዜ ‘አይሆንም ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የአሞንም ልጆች ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ሳለ፦ እንዲህ አይሁን፥ ነገር ግን ንጉሥ ይንገሥልን አላችሁኝ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 12:12
15 Referencias Cruzadas  

ጌዴ​ዎ​ንም፥ “እኔ አል​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ ልጄም አይ​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ዛ​ች​ኋል እንጂ” አላ​ቸው።


ዛሬ ግን ከመ​ከ​ራ​ች​ሁና ከጭ​ን​ቃ​ችሁ ሁሉ ያዳ​ና​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ችሁ፦ ‘እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን’ አላ​ች​ሁት። አሁ​ንም በየ​ነ​ገ​ዳ​ች​ሁና በየ​ወ​ገ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁሙ” አላ​ቸው።


ንጉ​ሥህ ወዴት አለ? በየ​ከ​ተ​ማህ ሁሉ እስኪ ያድ​ንህ! ንጉ​ሥና አለቃ ስጠኝ የም​ት​ለኝ እስኪ እነ​ርሱ ይበ​ቀ​ሉ​ልህ?


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነውና ቸል አይ​ለ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራ​ጃ​ችን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችን ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉ​ሣ​ችን ነው፤ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነ​ናል።


ልጆ​ቹም በመ​ን​ገዱ አል​ሄ​ዱም፤ ነገር ግን ረብ ለማ​ግ​ኘት ፈቀቅ አሉ፤ መማ​ለጃ በሉ፤ ፍርድ አደሉ።


እና​ን​ተም ዛሬ በአ​ባቴ ቤት ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል፤ ሰባ የሆ​ኑ​ትን ልጆ​ቹ​ንም በአ​ንድ ድን​ጋይ ላይ ገድ​ላ​ች​ኋል፤ ወን​ድ​ማ​ች​ሁም ስለ​ሆነ የዕ​ቅ​ብ​ቱን ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን በሰ​ቂማ ሰዎች ላይ አን​ግ​ሣ​ች​ኋል፥


በያ​ዕ​ቆብ ላይ ድካም የለም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕማም አይ​ታ​ይም፤ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነው፤ የአ​ለ​ቆ​ችም ክብር ለእ​ርሱ ነው።


ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል በት​ው​ል​ዳ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን አቆ​ማ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተና ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ አም​ላክ እሆን ዘንድ።


በሞ​ዓ​ብና በአ​ሞ​ንም ልጆች መካ​ከል፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ የነ​በሩ አይ​ሁድ ሁሉ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ እን​ዳ​ስ​ቀረ፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በላ​ያ​ቸው እንደ ሾመው ሰሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios