አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፤ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁ ጊዜ ግደሉት። አትፍሩም፤ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘዛቸው።
1 ጴጥሮስ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሕዛብ ፈቅደው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋዊ ምኞት፣ በስካር፣ በጭፈራ፣ ያለ ልክ በመጠጣት፣ በአስጸያፊ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብ እንደሚያደርጉት በመዳራት፥ በሥጋዊ ምኞት፥ በስካር፥ በመሶልሶል፥ ያለ ልክ በመጠጣት፥ በአስነዋሪ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሕዛብ እንደሚያደርጉት በስድነት፥ በፍትወት፥ በስካር፥ ቅጥ ባጣ ፈንጠዝያ፥ ያለ ልክ ጠጥቶ በመጨፈርና አጸያፊ በሆነ የጣዖት አምልኮ ያሳለፋችሁት ዘመን ይበቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና። |
አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፤ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁ ጊዜ ግደሉት። አትፍሩም፤ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘዛቸው።
አሳም ይህን ቃልና የነቢዩን የአዳድን ልጅ የአዛርያስን ትንቢት በሰማ ጊዜ ጸና፤ ከይሁዳና ከብንያምም ሀገር ሁሉ በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ከያዛቸው ከተሞች ርኵሰትን ሁሉ አስወገደ፤ በእግዚአብሔርም ቤት ፊት የነበረውን የእግዚአብሔርን መሠዊያ አደሰ።
እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ አላዋቆች ይሆናሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፤ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይበድላሉ፤ ይህም የዐይን ምትሐት ነው፤ በፍርድ ይሰናከላሉ።
በመቃብርም መካከል የሚተኙ፥ በዋሻ ውስጥ የሚያልሙ፥ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። የመሥዋዕታቸውን ደምና ዕቃቸውንም ሁሉ ያረክሳሉ።
አንተ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተዉ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ፤ አመለኩአቸውም፤ ሰገዱላቸውም፤ እነርሱም ትተውኛል፤ ሕጌንም አልጠበቁም፤
ምድሬንም በተጠሉ በጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኀጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”
ለዐመፀኛው ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ! ርኵሰታችሁ ሁሉ ይብቃችሁ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የእስራኤል አለቆች ሆይ! ይብቃችሁ፤ ግፍንና ዐመፅን አስወግዱ፤ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ፤ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አርቁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
የቀድሞውንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግዚአብሔር አሳልፎታል፤ ዛሬ ግን በመላው ዓለም ንስሓ እንዲገቡ ሰውን ሁሉ አዝዞአል።
በቀን እንደሚሆን በጽድቅ ሥራ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር፥ በዝሙትና በመዳራትም አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን።
ቀድሞም እናንተ አሕዛብ በነበራችሁ ጊዜ ዲዳዎች ጣዖታትን ታመልኩ እንደ ነበር፥ ጣዖትም በማምለክ ረክሳችሁ እንደ ነበር፥ ወደ ወሰዱአችሁም ትሄዱ እንደ ነበር ታውቃላችሁ።
እንግዲህ እናንተ እንዲህ ስትሆኑ እነማን ናችሁ? ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋልም።
ወይም እንደ ገና ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔር ያሳዝነኝ ይሆናል፤ በድለው ንስሓ ላልገቡም ስለ ርኵስነታቸውና ስለ መዳራታቸው፥ ስለሚሠሩት ዝሙታቸውም ለብዙዎች አዝን ይሆናል።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኀጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፤ ብቻውን ንጉሣችንንና ጌታችንንም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።