Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ጴጥሮስ 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በዚህም ነገር ወደዚያ መዳራት ብዛት ከእነርሱ ጋር ስለማትሮጡ እየተሳደቡ ይደነቃሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ይህን በመሰለ ብኩን ሕይወት ከእነርሱ ጋራ ስለማትሮጡ እንግዳ ሆኖባቸው በመደነቅ ይሰድቧችኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ይህን በመሰለ ብክነት ከእነርሱ ጋር ባለመተባበራችሁ ይደነቃሉ፤ ይሰድቡአችኋልም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አሁን ግን በዚህ ነገር አለመጠን ከእነርሱ ጋር በመቅበጥ ባለመሳተፋችሁ ይደነቃሉ፤ ይሰድቡአችኋልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በዚህም ነገር ወደዚያ መዳራት ብዛት ከእነርሱ ጋር ስለማትሮጡ እየተሳደቡ ይደነቃሉ፤

Ver Capítulo Copiar




1 ጴጥሮስ 4:4
11 Referencias Cruzadas  

በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።


ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።


እነ​ር​ሱም በተ​ቃ​ወ​ሙ​ትና በሰ​ደ​ቡት ጊዜ ልብ​ሱን አራ​ግፎ፥ “እን​ግ​ዲህ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ደማ​ችሁ በራ​ሳ​ችሁ ላይ ነው፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ ወደ አሕ​ዛብ እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው።


እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፤ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ።


አይ​ሁ​ድም የተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ውን ብዙ ሕዝብ ባዩ ጊዜ ቀኑ​ባ​ቸው፤ እየ​ተ​ሳ​ደ​ቡም ጳው​ሎስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ተቃ​ወሙ።


“ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፤” ደግሞ “የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች፤” እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።


እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤


በቀን እን​ደ​ሚ​ሆን በጽ​ድቅ ሥራ እን​መ​ላ​ለስ፤ በዘ​ፈ​ንና በስ​ካር፥ በዝ​ሙ​ትና በመ​ዳ​ራ​ትም አይ​ሁን፤ በክ​ር​ክ​ርና በቅ​ና​ትም አይ​ሁን።


ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ያ ትንሹ ልጁ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ በዚ​ያም በመ​ዳ​ራት እየ​ኖረ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ በተነ፤ አጠ​ፋም።


መዳ​ራት ነውና ወይን በመ​ጠ​ጣት አት​ስ​ከሩ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመሉ እንጂ።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios