2 ሳሙኤል 13:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፤ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁ ጊዜ ግደሉት። አትፍሩም፤ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘዛቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፣ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ ከዚያም እኔ አምኖንን፣ ‘ምቱት’ ስላችሁ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔ ነኝ አትፍሩ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ” ብሎ አዘዛቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ከዚያም አቤሴሎም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ እኔ ‘አምኖንን፥ ምቱት’ በምላችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔው ስለሆንኩ አትፍሩ፤ ብርቱዎች ሁኑ፥ ጨከን በሉም” ብሎ አዘዛቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 አገልጋዮቹንም “አምኖን ብዙ ጠጥቶ መስከሩን ተመልከቱ፤ እኔም ትእዛዝ በምሰጣችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ይህን ትእዛዝ የሰጠኋችሁ እኔ ስለ ሆንኩ ከቶ አትፍሩ! ደፋሮች ሁኑ፤ ምንም አታመንቱ!” አላቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፥ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፦ አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁም ጊዜ ግደሉት፥ አትፍሩም፥ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ ጽኑም ብሎ አዘዛቸው። Ver Capítulo |