የዳዊት ኀያላን ስም ይህ ነው። የሦስተኛው ክፍል አለቃ የሆነ ከነዓናዊው ኢያቡስቴ ነበረ፤ ጎራዴውን መዝዞ ስምንት መቶ ያህል ጭፍሮችን በአንድ ጊዜ የገደለ አሶናዊው አዲኖን ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 27:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆችና የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆችም ለንጉሡና ለንጉሡ ትእዛዝ ሁሉ የሚያገለግሉ ሹማምት እንደ ቍጥራቸው በየክፍላቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓመቱ ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል የቤተ ሰብ አለቆች፣ የሻለቆች፣ የመቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትን ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች የሺህ አለቆች የመቶ አለቆችም በክፍሎች ምደባ ሁሉ ንጉሡን ያገለገሉት ሹማምንት እንደ ቁጥራቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሀያ አራት ሺህ ሆነው በዓመት ውስጥ ባሉት ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በታች የተመለከተው የእስራኤላውያን የቤተሰብ አለቆችና የጐሣ መሪዎች፥ እንዲሁም ዓመቱን በሙሉ በየወሩ ንጉሡንና ሕዝቡን የሚያገለግሉ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆችና አዛዦቻቸው ስም ዝርዝር ነው። እያንዳንዱ ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆችና የሺህ አለቆች የመቶ አለቆችም በክፍሎች ነገር ሁሉ ንጉሡን ያገለገሉትም ሹማምት እንደ ቍጥራቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓመት ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር። |
የዳዊት ኀያላን ስም ይህ ነው። የሦስተኛው ክፍል አለቃ የሆነ ከነዓናዊው ኢያቡስቴ ነበረ፤ ጎራዴውን መዝዞ ስምንት መቶ ያህል ጭፍሮችን በአንድ ጊዜ የገደለ አሶናዊው አዲኖን ነበረ።
እነዚያም ሹሞች እያንዳንዱ በየወሩ ንጉሡን ሰሎሞንንና ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ማዕድ የሚቀርቡትን ሁሉ ይቀልቡ ነበር፤ ምንም አያጐድሉም ነበር።
ሰሎሞንም ለንጉሡና ለቤተሰቡ ቀለብ የሚሰጡ በእስራኤል ሁሉ ላይ ዐሥራ ሁለት ሹሞችን ሾመ። ከዓመቱ ውስጥ እያንዳንዱን ወር እያንዳንዳቸው ይቀልቡ ነበር።
በየወሩም እያፈራረቀ ወደ ሊባኖስ ዐሥር ዐሥር ሺህ ይልክ ነበር፤ አንድ ወርም በሊባኖስ፥ ሁለት ወርም በቤታቸው ይቀመጡ ነበር። አዶኒራምም የገባሪዎች አለቃ ነበረ።
ለዳዊትም የነበሩት ኀያላን አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ስለ እስራኤል እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ያነግሡት ዘንድ ከእስራኤል ሁሉ ጋር በመንግሥቱ አጸኑት።
ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ቃል ሁሉና በንጉሡ ትእዛዝ ሁሉ በሮቤላውያንና በጋዳውያን፥ በምናሴም ነገድ እኩሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው።
ለመጀመሪያው ወር በአንደኛው ክፍል ላይ የዘብድኤል ልጅ ያሶብአም ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉና የፍርድ አለቆችን፥ ንጉሡንም በየተራ የሚጠብቁትን አለቆቹን፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሡና በልጆቹ ሀብትና ንብረት ላይ፥ መባ ባለበት ላይ የተሾሙትን ጃንደረቦችንም፥ ኀያላኑንና ሰልፈኞቹን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
የአባቶችም ቤቶች አለቆች፥ የእስራኤልም ልጆች አለቆች፥ ሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ በእግዚአብሔር ቤት ሥራ የተሾሙና የንጉሡ ግንበኞች በፈቃዳቸው አቀረቡ።
ሰሎሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች ለመቶ አለቆችም፥ ለፈራጆችም፥ በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ሁሉ ተናገረ።
ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳም አለቆች፥ የዐሥርም አለቆች አድርጎ ሾማቸው።
አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።
ከእናንተም ጥበበኞችና ዐዋቂዎች፥ አስተዋዮችም የሆኑትን ሰዎች ወሰድሁ፤ በእናንተም ላይ አለቆች፥ የሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ የአምሳ አለቆችም፥ የዐሥር አለቆችም፥ ለፈራጆቻችሁም ጻፎች አድርጌ ሰየምኋቸው።
እንዲህም ሆነ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ፥ እግዚአብሔርም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ካሳረፈ በኋላ፥ ኢያሱ ሸመገለ፤ ዘመኑም ዐለፈ፤
ለራሱም የሻለቆችና የመቶ አለቆች የአምሳ አለቆችም ያደርጋቸዋል፤ እርሻውንም የሚያርሱ፥ እህሉንም የሚያጭዱ፥ ፍሬውንም የሚለቅሙ፥ የጦር መሣሪያውንና የሰረገሎቹንም ዕቃ የሚሠሩ ያደርጋቸዋል።