1 ዜና መዋዕል 27:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ከዚህ በታች የተመለከተው የእስራኤላውያን የቤተሰብ አለቆችና የጐሣ መሪዎች፥ እንዲሁም ዓመቱን በሙሉ በየወሩ ንጉሡንና ሕዝቡን የሚያገለግሉ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆችና አዛዦቻቸው ስም ዝርዝር ነው። እያንዳንዱ ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 የእስራኤል የቤተ ሰብ አለቆች፣ የሻለቆች፣ የመቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትን ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች የሺህ አለቆች የመቶ አለቆችም በክፍሎች ምደባ ሁሉ ንጉሡን ያገለገሉት ሹማምንት እንደ ቁጥራቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሀያ አራት ሺህ ሆነው በዓመት ውስጥ ባሉት ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆችና የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆችም ለንጉሡና ለንጉሡ ትእዛዝ ሁሉ የሚያገለግሉ ሹማምት እንደ ቍጥራቸው በየክፍላቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓመቱ ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆችና የሺህ አለቆች የመቶ አለቆችም በክፍሎች ነገር ሁሉ ንጉሡን ያገለገሉትም ሹማምት እንደ ቍጥራቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓመት ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር። Ver Capítulo |
ለእያንዳንዱም ወር የቡድን መሪ የነበሩት ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው ነው፦ በመጀመሪያው ወር በአንደኛው ክፍል የበላይ የሆነው የዛብዲኤል ልጅ ያሾብዓም ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ፤ እርሱም የይሁዳ ነገድ ክፍል የሆነው የፋሬስ ጐሣ አባል ነበር። በሁለተኛው ወር ክፍል ላይ የበላይ የነበረው አሖሓዊው ዶዳይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ፤ ሚቅሎትም የእርሱ ምክትል ነበር። በሦስተኛው ወር ሦስተኛው የሠራዊት አለቃ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ ይህ በናያ በሠላሳው መካከል ኀያል ሆኖ የሠላሳው አለቃ ነበረ። ልጁ ዓሚዛባድ የክፍሉ አዛዥ ነበር። በአራተኛው ወር በአራተኛው ክፍል የበላይ የሆነው የኢዮአብ ወንድም ዐሣሄል ነበር። ልጁም ዜባድያ የእርሱ ተተኪ ሆነ። በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በአምስተኛው ወር፥ በአምስተኛው ክፍል የበላይ ይጅሃራዊው ሻምሁት ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በስድስተኛው ወር፥ በስድስተኛው ክፍል የበላይ ተቆዓዊው የዒቄሽ ልጅ ዒራ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በሰባተኛው ወር፥ በሰባተኛው ክፍል የበላይ ከኤፍሬም ነገድ ፐሎናዊ የሆነው ሔሌጽ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በስምንተኛው ወር፥ በስምንተኛው ክፍል የበላይ የሑሻ ተወላጅ የነበረው ሲበካይ ነበር፤ እርሱም የይሁዳ ነገድ ከነበረው ከዛራ ዘር ነበር። በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በዘጠነኛው ወር፥ በዘጠነኛው ክፍል የበላይ ከብንያም ነገድ የነበረው ዓናቶታዊው አቢዔዜር ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በዐሥረኛው ወር፥ በዐሥረኛው ክፍል የበላይ ከዛራ ነገድ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው ማሕራይ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በዐሥራ አንደኛው ወር፥ በዐሥራ አንደኛው ክፍል የበላይ ከኤፍሬም ተወላጅ ነገድ የጆርቶን ተወላጅ በናያ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በዐሥራ ሁለተኛው ወር በዐሥራ ሁለተኛው ክፍል የበላይ የዖትኒኤል ጐሣ የነጦፋ ተወላጅ የነበረው ሔልዳይ ነበር። በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ።