Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 27:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች የሺህ አለቆች የመቶ አለቆችም በክፍሎች ምደባ ሁሉ ንጉሡን ያገለገሉት ሹማምንት እንደ ቁጥራቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሀያ አራት ሺህ ሆነው በዓመት ውስጥ ባሉት ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የእስራኤል የቤተ ሰብ አለቆች፣ የሻለቆች፣ የመቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትን ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በታች የተመለከተው የእስራኤላውያን የቤተሰብ አለቆችና የጐሣ መሪዎች፥ እንዲሁም ዓመቱን በሙሉ በየወሩ ንጉሡንና ሕዝቡን የሚያገለግሉ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆችና አዛዦቻቸው ስም ዝርዝር ነው። እያንዳንዱ ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችና የሺህ አለ​ቆች፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም ለን​ጉ​ሡና ለን​ጉሡ ትእ​ዛዝ ሁሉ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ሹማ​ምት እንደ ቍጥ​ራ​ቸው በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ። እነ​ዚ​ህም ክፍ​ሎች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓ​መቱ ወራት ሁሉ በየ​ወሩ ይገ​ቡና ይወጡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆችና የሺህ አለቆች የመቶ አለቆችም በክፍሎች ነገር ሁሉ ንጉሡን ያገለገሉትም ሹማምት እንደ ቍጥራቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓመት ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 27:1
18 Referencias Cruzadas  

የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፤ የታሕክሞን ሰው ዮሼብ ባሼቤት የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፥ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው በአንዴ የገደለ ነው።


ለሰሎሞንና በቤተ መንግሥቱ ለሚቀለቡት ሁሉ የሚያስፈልገውን ምግብ የሚያቀርቡት ዐሥራ ሁለቱ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች እያንዳንዳቸው በተመደበላቸው ወር ምንም ነገር ሳያጓድሉ በወቅቱ ያመጡ ነበር።


ሰሎሞን በመላው እስራኤል ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችን ሾመ፤ የእነርሱም ተግባር ከየግዛታቸው ለንጉሡና ለንጉሡ ቤተሰብ ቀለብ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ማቅረብ ነበር፤ እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው።


በእነርሱ ላይ አዶኒራም የተባለውን ሰው ኀላፊ አድርጎ ሾመ፤ ሠራተኞቹንም ዐሥር ዐሥር ሺህ አድርጎ በሦስት ቡድን በመክፈል እያንዳንዱ ቡድን ተራ ገብቶ አንድ ወር በሊባኖስ እንዲሠራ፥ ሁለት ወር ደግሞ በቤቱ እንዲያርፍ ወሰነ።


ለዳዊትም የነበሩት የኃያላን አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ስለ እስራኤል እንደ ተናገረው እንደ ጌታ ቃል ሊያነግሡት ከእስራኤል ሁሉ ጋር በመንግሥቱ ላይ አጸኑት።


ዳዊትም ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ከሹማምንቱም ሁሉ ጋር ተማከረ።


ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት ለእግዚአብሔር ጉዳይ ሁሉና ለንጉሡ ጉዳይ በሮቤላውያንና በጋዳውያን በምናሴም ነገድ እኩሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው።


ለመጀመሪያው ወር የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም በአንደኛው ክፍል ላይ ተሹሞ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ውስጥ ሀያ አራት ሺህ አባላት ነበሩ።


ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉ፥ የነገዶቹንም አለቆች፥ ንጉሡንም በክፍል የሚያገለግሉትን የሠራዊቱ አለቆች፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሥና በልጆቹ ሀብትና ግዛት ላይ የተሾሙትን፥ ጃንደረቦችንም፥ ጽኑዓን ኃያላኑንም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።


የአባቶችም ቤቶች አለቆች፥ የእስራኤልም ነገዶች አለቆች፥ ሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ በንጉሡም ሥራ ላይ የተሾሙት በፈቃዳቸው አቀረቡ።


ሰሎሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለፈራጆችም፥ በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ።


ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ መስራት የሚችሉ ሰዎችን መረጠ፥ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳ አለቆች፥ የዐሥር አለቆች አድርጎ ሾማቸው።


ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ከዚህ በኋላ የቀሩት ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።


እኔም ጥበበኞችና አዋቂዎች የሆኑትን የነገዶቻችሁን አለቆች ተቀበልኩ፥ በእናንተም ላይ የሺህ አለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ የኀምሳ አለቆችም፥ የዐሥር አለቆችም ገዢዎችም በየነገዶቻቸው አደረግኋቸው።


እንዲህም ሆነ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ፥ ጌታም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ባሳረፋቸው ጊዜ፥ ኢያሱም በሸመገለ ዕድሜውም በገፋ ጊዜ፥


አንዳንዶቹን ሻለቆችና አምሳ አለቆች ያደርጋቸዋል፤ ሌሎቹን መሬቱን እንዲያርሱና እህሉን እንዲያጭዱ፥ ሌሎቹን ደግሞ የጦር መሣሪያና ለሠረገላ የሚሆኑትን ዕቃዎች እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos