1 ዜና መዋዕል 27:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ለመጀመሪያው ወር በአንደኛው ክፍል ላይ የዘብድኤል ልጅ ያሶብአም ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 በመጀመሪያው ወር፣ የመጀመሪያው ዋና ክፍል የበላይ የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም ሲሆን፣ በሥሩ የሚታዘዙ ሃያ አራት ሺሕ ሰዎች ነበሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ለመጀመሪያው ወር የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም በአንደኛው ክፍል ላይ ተሹሞ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ውስጥ ሀያ አራት ሺህ አባላት ነበሩ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2-15 ለእያንዳንዱም ወር የቡድን መሪ የነበሩት ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው ነው፦ በመጀመሪያው ወር በአንደኛው ክፍል የበላይ የሆነው የዛብዲኤል ልጅ ያሾብዓም ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ፤ እርሱም የይሁዳ ነገድ ክፍል የሆነው የፋሬስ ጐሣ አባል ነበር። በሁለተኛው ወር ክፍል ላይ የበላይ የነበረው አሖሓዊው ዶዳይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ፤ ሚቅሎትም የእርሱ ምክትል ነበር። በሦስተኛው ወር ሦስተኛው የሠራዊት አለቃ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ ይህ በናያ በሠላሳው መካከል ኀያል ሆኖ የሠላሳው አለቃ ነበረ። ልጁ ዓሚዛባድ የክፍሉ አዛዥ ነበር። በአራተኛው ወር በአራተኛው ክፍል የበላይ የሆነው የኢዮአብ ወንድም ዐሣሄል ነበር። ልጁም ዜባድያ የእርሱ ተተኪ ሆነ። በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በአምስተኛው ወር፥ በአምስተኛው ክፍል የበላይ ይጅሃራዊው ሻምሁት ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በስድስተኛው ወር፥ በስድስተኛው ክፍል የበላይ ተቆዓዊው የዒቄሽ ልጅ ዒራ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በሰባተኛው ወር፥ በሰባተኛው ክፍል የበላይ ከኤፍሬም ነገድ ፐሎናዊ የሆነው ሔሌጽ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በስምንተኛው ወር፥ በስምንተኛው ክፍል የበላይ የሑሻ ተወላጅ የነበረው ሲበካይ ነበር፤ እርሱም የይሁዳ ነገድ ከነበረው ከዛራ ዘር ነበር። በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በዘጠነኛው ወር፥ በዘጠነኛው ክፍል የበላይ ከብንያም ነገድ የነበረው ዓናቶታዊው አቢዔዜር ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በዐሥረኛው ወር፥ በዐሥረኛው ክፍል የበላይ ከዛራ ነገድ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው ማሕራይ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በዐሥራ አንደኛው ወር፥ በዐሥራ አንደኛው ክፍል የበላይ ከኤፍሬም ተወላጅ ነገድ የጆርቶን ተወላጅ በናያ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። በዐሥራ ሁለተኛው ወር በዐሥራ ሁለተኛው ክፍል የበላይ የዖትኒኤል ጐሣ የነጦፋ ተወላጅ የነበረው ሔልዳይ ነበር። በእርሱም ክፍል ኻያ አራት ሺህ ተረኞች ነበሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ለመጀመሪያው ወር በአንደኛው ክፍል ላይ የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። Ver Capítulo |