ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሕፃኑ በሕይወት ሳለ መጾሜና ማልቀሴ እርግጥ ነው፤ እግዚአብሔር ምሕረት አድርጎልኝ ሕፃኑ እንዳይሞት ያደርግ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር፤
ሶፎንያስ 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትእዛዞቹን የምትፈጽሙ፥ በምድሪቱ የምትኖሩ፥ እናንተ ትሑታን ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ የጽድቅን ሥራ ሥሩ፤ በትሕትናም ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ በዚህም ሁኔታ እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት ቀን ምናልባት ከቅጣት ታመልጡ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የምድር ትሑታን ሁሉ፣ ትእዛዙን የምትፈጽሙ፣ እግዚአብሔርን እሹ፤ ጽድቅንና ትሕትናን ፈልጉ፤ በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ትሰወሩ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ፥ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ ጌታን ፈልጉ፤ ጽድቅን ፈልጉ፥ ትሕትናን ፈልጉ፤ ምናልባት በጌታ ቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ፣ ምናልባት በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፥ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ፥ ምናልባት በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል። |
ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሕፃኑ በሕይወት ሳለ መጾሜና ማልቀሴ እርግጥ ነው፤ እግዚአብሔር ምሕረት አድርጎልኝ ሕፃኑ እንዳይሞት ያደርግ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር፤
እናንተም እንዲህ ብላችሁ ትመልሱላቸዋላችሁ፤ ‘ይህ እግዚአብሔርን ለማክበር የሚደረግ የፋሲካ መሥዋዕት ነው፤ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር የእስራኤላውያንን መኖሪያ ቤቶች አልፎ በመሄድ ግብጻውያንን ሲገድል እኛን አድኖናል።’ ” እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ ተንበርክከው ሰገዱ፤
መልካም ማድረግንም ተማሩ፤ ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ የተጨቈኑትን ታደጉ፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት ጠብቁ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ ስሙ።”
ነገር ግን በእውነት ለድኾች ይፈርዳል፤ ረዳት ለሌላቸውም ወገኖች ተከላካይ በመሆን መብታቸውን ያስከብራል፤ በበትር እንደሚመታ፥ መረን በተለቀቁት ላይ ይፈርዳል፤ በቃሉም ክፉዎችን ያጠፋል።
ለተጨቈኑት መልካም ዜናን አበሥር ዘንድ፥ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩት ነጻነትን፥ ለታሰሩት መፈታትን ለማወጅ እግዚአብሔር ቀብቶ ስለ ላከኝ፥ የጌታ እግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው።
ታዲያ አንተ ለራስህ የተለየ መልካም ነገር እንዳደርግልህ ትፈልጋለህን? ይህን መፈለግ የለብህም፤ እኔ መቅሠፍትን በሰው ዘር ሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ ይሁን እንጂ በምትሄድበት ቦታ ሁሉ ሌላው ቢቀር ሕይወትህ እንድትተርፍ አደርጋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እኔም ‘እንግዲህ ዕዳሪውን መሬት ዕረሱ፤ ጽድቅን ለራሳችሁ ዝሩ፤ የማይለዋወጥ ፍቅርን ሰብስቡ፤ እነሆ ወደ እኔ ወደ አምላካችሁ የምትመለሱበት ጊዜ አሁን ነው! እኔም መጥቼ ፍትሕን አሰፍንላችኋለሁ’ አልኩ።
“በአራተኛው፥ በአምስተኛው፥ በሰባተኛውና በዐሥረኛው ወር ትጠብቁት የነበረው ጾም ሁሉ ለይሁዳ ሕዝብ የተድላና የደስታ በዓል ይሆንላቸዋል፤ እናንተ ግን እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”
በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መኖር እንደሚገባችሁ ከእኛ ተምራችኋል፤ አሁንም የምትኖሩት እንዲሁ ነው፤ በጌታ በኢየሱስ ስም የምንለምናችሁና የምንመክራችሁም ከዚህ በፊት ካደረጋችሁት ይበልጥ እንድታደርጉ ነው።
ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጭምትነት መንፈስ ያጌጠው፥ በልብ ተሰውሮ የሚገኘው፥ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን።
ይልቅስ በጌታችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እርሱንም በማወቅ ከፍ ከፍ በሉ፤ ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።