Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ጴጥሮስ 1:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እንግዲህ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን ስላነጻችሁ፣ ለወንድሞቻችሁ ቅን ፍቅር ይኑራችሁ፤ እርስ በርሳችሁም አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ ለወንድማማች እውነተኛ ፍቅር፥ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደደ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።

Ver Capítulo Copiar




1 ጴጥሮስ 1:22
51 Referencias Cruzadas  

የዚህ ትእዛዝ ዓላማ ግን ከንጹሕ ልብ፥ ከመልካም ኅሊና፥ ከእውነተኛ እምነት የሚገኝ ፍቅር ነው።


ሁልጊዜ የእርስ በርስ የወንድማማችነት ፍቅር ይኑራችሁ፤


እግዚአብሔርን ያየው ማንም ሰው የለም። እኛ እርስ በርሳችን ብንፋቀር እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፤ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል።


ወዳጆች ሆይ! ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ እርስ በርሳችን እንፋቀር፤ የሚያፈቅር ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል።


በቀረውስ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ በመስማማት ኑሩ፤ የሌላውን ሰው ችግር እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ደጎችና ትሑቶች ሁኑ።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል፤ እናንተ ኃጢአተኞች! እጆቻችሁን አጽዱ፤ እናንተ ወላዋዮች! ልባችሁን አጥሩ።


የእግዚአብሔር ትእዛዝ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድናምንና ክርስቶስ ባዘዘንም መሠረት እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ነው።


ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ማመስገንም ተገቢያችን ነው፤ የምናመሰግነውም እምነታችሁ ይበልጥ እያደገና የእያንዳንዳችሁ የእርስ በርስ ፍቅር እየጨመረ በመሄዱ ነው።


እኛ እንደምናፈቅራችሁ ጌታ እርስ በርስና ለሌሎችም ሁሉ ያላችሁ ፍቅር እንዲያድግና እንዲበዛ ያድርግላችሁ፤


እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን የሚጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ከሆነ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልም።


ሰውን ሁሉ አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


ልባቸውን በእምነት ስላነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል ምንም ልዩነት አላደረገም።


ከመጀመሪያው የሰማችሁት መልእክት “እርስ በርሳችን እንፋቀር” የሚል ነው።


እግዚአብሔርን በማምለክ ላይ የወንድማማችነት መዋደድን፥ በወንድማማችነት መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ።


ፍቅራችሁ ዕውቀትና ማስተዋል የሞላበት ሆኖ እያደገ እንዲሄድ እጸልያለሁ።


በሰላም ተሳስራችሁ ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚገኘውን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።


እኛ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ የጽድቅን ተስፋ በእምነት እንጠባበቃለን።


ነገር ግን አንድ የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ ይኸውም የቀድሞውን ፍቅርህን ትተሃል፤


ፍርድ የሚጀመርበት ጊዜ ቀርቦአል፤ ፍርዱ የሚጀመረውም በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ ነው፤ ታዲያ፥ ፍርድ የሚጀመረው በእኛ ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?


ፍቅር ብዙ ኃጢአትን ስለሚሸፍን ከሁሉ በላይ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው።


በዘለዓለም መንፈስ አማካይነት ራሱን ነውር የሌለበት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እንድናገለግል ኅሊናችንን ከሞተ ሥራ እንዴት ይበልጥ ያነጻ ይሆን!


እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ ነው፤ ስለዚህ ሥራችሁንና በፊትም ሆነ አሁን ቅዱሳንን በመርዳት ስለ ስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም።


እንዲሁም በንጽሕና፥ በዕውቀት፥ በትዕግሥት፥ በደግነት፥ በመንፈስ ቅዱስ በመመራትና ግብዝነት በሌለበት ፍቅር፥


እንግዲህ እኔ የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።


እንዲሁም እናንተ ሚስቶች! ለባሎቻችሁ ታዘዙ፤ በዚህ ዐይነት አንዳንዶች በእግዚአብሔር ቃል የማያምኑ ቢሆኑም እንኳ ያለ ቃሉ ትምህርት በሚስቶቻቸው ጠባይ ብቻ ሊሳቡ ይችሉ ይሆናል።


ፍጹም ሆኖ ከተገኘም በኋላ ለሚታዘዙት ሁሉ ለዘለዓለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።


በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተሰጠህን መልካም ዐደራ ጠብቅ።


አሮጊቶችን እንደ እናቶች አድርገህ ተመልከታቸው፤ እንዲሁም ወጣት ሴቶችን እንደ እኅቶች አድርገህ በፍጹም ንጽሕና ተመልከታቸው።


ወጣት በመሆንህ ማንም አይናቅህ፤ ይልቅስ በንግግር፥ በኑሮ፥ በፍቅር፥ በእምነትና በንጽሕና ለአማኞች መልካም ምሳሌ ሁን።


ወደ መቄዶንያ ስሄድ ሳለሁ ዐደራ እንዳልኩህ እዚያ ያሉ አንዳንድ ሰዎች የሐሰት ትምህርት እንዳያስተምሩ ታደርጋቸው ዘንድ በኤፌሶን ተቀመጥ።


በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ማመስገን ይገባናል፤ የምናመሰግነውም እናንተ በመንፈስ ቅዱስ በመቀደሳችሁና እውነትን በማመናችሁ እንድትድኑ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ስለ መረጣችሁ ነው።


እናንተ ሞኞች የገላትያ ሰዎች! ማን አፍዝ አደንግዝ አደረገባችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ ተሰቅሎ በፊት ለፊታችሁ በግልጥ ይታይ ነበር።


ደኅና ትራመዱ ነበር፤ ታዲያ አሁን ለእውነት እንዳትታዘዙ የከለከላችሁ ማን ነው?


በሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞታላችሁ፤ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ሥጋዊ ሥራችሁን ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ።


የራሳቸውን ጥቅም በሚፈልጉ፥ ለእውነት በማይታዘዙና ለዐመፅ በሚታዘዙ ዐድመኞች ላይ ግን የእግዚአብሔር ቊጣና መቅሠፍት ይመጣባቸዋል።


ስለ ክርስቶስ ስም አሕዛብ ሁሉ እንዲያምኑና እንዲታዘዙ ለማድረግ በእርሱ አማካይነት ለሐዋርያነት የሚያበቃንን ጸጋ ተቀብለናል።


በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው።


እናንተም ስለ ነገርኳችሁ ቃል አሁን ንጹሖች ናችሁ።


በዚህ ሁኔታ የእግዚአብሔር ቃል እየተስፋፋ ስለ ሄደ፥ በኢየሩሳሌም የአማኞች ቊጥር በጣም እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም እጅግ ብዙዎቹ አመኑ።


እነርሱ በእውነት ቅዱሳን እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ ቅዱስ አደርጋለሁ።


ስለዚህ ርኲሰትንና የክፋትንም ብዛት ሁሉ አስወግዳችሁ እግዚአብሔር በልባችሁ የተከለውንና ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።


እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ በዐቀደው መሠረት ለተመረጣችሁት፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመታዘዝና በደሙ ተረጭታችሁ ለመንጻት በመንፈስ ቅዱስ ለተቀደሳችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።


እነዚህ በወህኒ ቤት የነበሩ መናፍስት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው ሳለ አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በዚያ መርከብ ውስጥ ገብተው በውሃ አማካይነት የዳኑት ቊጥራቸው ስምንት የሆነ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios