መዝሙር 88:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዳኜ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ትረዳኝ ዘንድ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ሌሊቱንም በአንተ ፊት አለቅሳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዳኜ የሆንህ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በቀንና በሌሊት በፊትህ እጮኻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር። ለመዘምራን አለቃ በማኸላት ለመዘመር፥ የይዝራኤላዊው የኤማን ትምህርት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ምሕረትህን ለዘለዓለም እዘምራለሁ። ጽድቅህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ። |
እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ፤ ከኤዝራሐዊው ኤታን፥ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሄማን፥ ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጐረቤት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ፤
ሰሎሞንም በበኩሉ በኪራም ቤተ መንግሥት ውስጥ ላሉት ሰዎች ቀለብ የሚሆን ሁለት ሺህ ቶን ስንዴና አራት መቶ ሺህ ሊትር ንጹሕ የወይራ ዘይት በየዓመቱ ይሰጥ ነበር።
እግዚአብሔር ሆይ! አገልጋዮችህ ስለ ሆኑት የእስራኤል ሕዝብ ደኅንነት ቀንና ሌሊት የማቀርበውን ጸሎቴን ስማ፤ እኔንም አስበኝ፤ እኛ እስራኤላውያን የሠራነውንም ኃጢአት እናዘዛለሁ፤ በእርግጥም እኔና የቀድሞ አባቶቼ በደል ሠርተናል።
አምላኬና አዳኜ ሆይ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ፤ ተቈጥተህም እኔን አገልጋይህን ከአንተ እንድርቅ አታድርገኝ፤ ረዳቴም ስለ ሆንክ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም።
ሞኞች በልባቸው “እግዚአብሔር የለም” ይላሉ፤ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች የተበላሹ ናቸው፤ አጸያፊ ድርጊቶችንም ይፈጽማሉ፤ ከእነርሱ መካከል መልካም ነገርን የሚያደርግ አንድም የለም።
ጸሎታችንን ሰምተህ ድልን ታጐናጽፈናለህ፤ እኛንም ለማዳን ብዙ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ፤ ሩቅ ከሆነው ባሕር ማዶ ያሉት ሳይቀሩ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይታመናሉ።
በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል።
ከዚህም በኋላ ዕድሜዋ ሰማኒያ አራት ዓመት እስኪሆን ድረስ ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በጾምና በጸሎት ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ታገለግል ነበር።
ገንዘባቸውንም እንዳይሰርቁአቸው ምከራቸው፤ ይልቅስ የአዳኛችን የእግዚአብሔር ትምህርት በሁሉ ነገር እንዲከበር ሁልጊዜ ፍጹም ታማኝነትን ያሳዩ።