Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ቲቶ 2:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በዚህ ዐይነት የተባረከውን ተስፋችንን እንዲሁም የታላቁ አምላካችንን፥ የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በክብር መገለጥ እንጠባበቃለን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ይህም የተባረከ ተስፋችን የሆነውን የታላቁን የአምላካችንንና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ በመጠባበቅ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እንዲሁም የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እንድንጠብቅ ያስተምረናል፤

Ver Capítulo Copiar




ቲቶ 2:13
42 Referencias Cruzadas  

ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።


የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ሆኖ ከመላእክቱ ጋር ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይከፍለዋል።


“የሰው ልጅ በመላእክቱ ሁሉ ታጅቦ በክብር ሲመጣ በክብር ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል፤


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አንተ እንዳልከው ነው፤ ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ታዩታላችሁ፤ እንዲሁም በሰማይ ደመና ሆኖ ሲመጣ ታዩታላችሁ እላችኋለሁ።”


ኢየሱስም “አዎ፥ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ታያላችሁ! እንዲሁም በሰማይ ደመና ተመልሶ ሲመጣ ታያላችሁ” አለ።


በዚህ በከሐዲና በኃጢአተኛ ትውልድ ፊት በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ እኔም የሰው ልጅ በአባቴ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር ስመጣ በእርሱ አፍርበታለሁ።”


እነርሱም ተስፋ እንደሚያደርጉት እኔም ጻድቃንና ኃጥአን ከሞት እንደሚነሡ በእግዚአብሔር ተስፋ አደርጋለሁ።


ተስፋችሁ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እያደገ እንዲሄድ የተስፋ አምላክ በእርሱ በመታመናችሁ ደስታንና ሰላምን በሙላት ይስጣችሁ።


በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ሞላ ተስፋው አያሳፍርም።


የአሁኑ ጊዜ መከራ ወደፊት ለእኛ ከሚገለጥልን ክብር ጋር ቢመዛዘን በምንም ሊተካከል እንደማይችል አድርጌ እቈጥረዋለሁ።


ስለዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በመጠባበቅ ስትኖሩ ምንም ዐይነት መንፈሳዊ ስጦታ አይጐድልባችሁም፤


የዚህ ዓለም ገዢ የሆነው ሰይጣን የማያምኑትን ሰዎች ልብ አሳወረው፤ በዚህም በእግዚአብሔር መልክ የተገለጠው የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል የሚያበራላቸውን ብርሃን እንዳያዩ አደረጋቸው።


“ብርሃን በጨለማ ውስጥ ይብራ!” ብሎ የተናገረ እግዚአብሔር በክርስቶስ መልክ የሚያበራውን የእግዚአብሔርን ክብር የማወቅ ብርሃን እንዲሰጠን ብርሃኑን በልባችን ውስጥ እንዲበራ አደረገ።


ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።


እግዚአብሔርም ለቅዱሳኑ ሊገልጥላቸው የፈቀደው ያለውን የዚህን ምሥጢር የክብር ብልጽግና በእናንተ በአሕዛብ መካከል ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ነው። ይህም ምሥጢር በተስፋ የምንጠባበቀው ክብር የሚገኝበት ክርስቶስ በእናንተ መካከል መሆኑ ነው።


የእውነት ቃል የሆነው ወንጌል በመጀመሪያ ወደ እናንተ በደረሰ ጊዜ በእርሱ ያለውን ተስፋ ሰምታችኋል፤ ስለዚህ እምነታችሁና ፍቅራችሁ የተመሠረተው በሰማይ ተዘጋጅቶ በሚቈያችሁ በዚህ ተስፋ ላይ ነው።


ሕይወታችሁ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።


ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን፥ በጸጋውም የዘለዓለም መጽናናትን፥ መልካም ተስፋንም የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን


ከዚህ በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚያጠፋውና በግርማ መምጣቱ የሚደመስሰው የዐመፅ ሰው ይገለጣል።


በአዳኛችን በእግዚአብሔር፥ በተስፋችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ከጳውሎስ፦


ለተወደድከው ልጄ ለጢሞቴዎስ፥ ከእግዚአብሔር አብና ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ለአንተ ይሁን።


በእግዚአብሔርና እንዲሁም መንግሥቱን በሚያቋቁምበት ጊዜ፥ በሕያዋንና በሙታን ላይ በሚፈርደው በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ዐደራ እልሃለሁ፤


ከእንግዲህ ወዲህ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ይህንንም አክሊል ያ ትክክለኛ ፍርድን ፈራጁ ጌታ በዚያን ቀን ይሰጠኛል፤ የሚሰጠውም ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእርሱን መገለጥ ለሚወድዱ ሁሉ ነው።


ይህም እምነት በዘለዓለም ሕይወት ተስፋ ላይ የተመሠረተ ነው፤ የማይዋሸው አምላክ ይህን ሕይወት ለመስጠት ከዘመናት በፊት ቃል ገባልን።


የጋራችን በሆነው እምነት በእውነት ልጄ ለሆንከው ለቲቶ፥ ከእግዚአብሔር አብና ከአዳኛችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለአንተ ይሁን።


ነገር ግን የመድኀኒታችን የእግዚአብሔር ደግነትና ፍቅር የተመላ ርኅራኄ በተገለጠ ጊዜ፥


እንዲሁም ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ አንድ ጊዜ ተሠውቶአል፤ ደግሞም ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን እርሱን የሚጠባበቁትን ለማዳን ሁለተኛ ጊዜ ይገለጣል።


ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤


ይህ ፈተና የሚደርስባችሁ የእምነታችሁን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው፤ የሚጠፋ ወርቅ እንኳ በእሳት ይፈተናል፤ ከወርቅ ይልቅ የከበረ እምነታችሁ እንደዚሁ መፈተን አለበት፤ ይህም የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፥ ክብርንና ውዳሴን ያስገኝላችኋል።


የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጽድቅ አማካይነት እኛ እንዳገኘነው እምነት ያለ የከበረ እምነት ላገኛችሁት፤


ይልቅስ በጌታችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እርሱንም በማወቅ ከፍ ከፍ በሉ፤ ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።


አብ የዓለም አዳኝ አድርጎ ወልድን እንደ ላከው አይተናል፤ እንመሰክራለንም።


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በምሕረቱ ወደ ዘለዓለም ሕይወት እንዲያደርሳችሁ በመጠባበቅ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ጠብቁት።


እነሆ በደመና ይመጣል፤ የወጉት ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ሰው ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤ ይህ ነገር እውነት ነው፤ አሜን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios