አምላክ ሆይ! ስእለቴን ሰማህ፤ አንተን ለሚፈሩ ሰዎች ያዘጋጀኸውን በረከት ለእኔም ሰጠኸኝ።
አምላክ ሆይ፤ ስእለቴን ሰምተሃልና፤ ስምህን የሚፈሩትንም ሰዎች ርስት ለእኔ ሰጠህ።
በድንኳንህ ለዘለዓለም እኖራለሁ፥ በክንፎችህም ጥላ እጋረዳለሁ፥
ነገር ግን ነፍሴ፥ ለእግዚአብሔር ትገዛለች፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
የሚፈሩትን ሁሉ፥ ታላላቆችንም ሆነ ታናናሾችን ይባርካል።
የዐይን ብሌን በጥንቃቄ የሚጠበቀውን ያኽል ጠብቀኝ፤ በጥበቃህ ውስጥ ሰውረኝ።
አምላክ ሆይ! እኔ ራሴ ለአንተ የስእለት ግዴታ ገብቼአለሁ፤ ስእለቴን ከምስጋና መሥዋዕት ጋር አቀርባለሁ።
አምላክ ሆይ! በጽዮን ሆነን አንተን ማመስገን፤ ለአንተ የተሳልነውንም መስጠት ይገባናል።
አሁን ግን በእርግጥ እግዚአብሔር ሰምቶኛል፤ የልመናዬንም ድምፅ አድምጦአል።
እግዚአብሔር ሆይ! የእውነት መንገድህን እከተል ዘንድ አስተምረኝ፤ ባልተከፋፈለ ልብም እንዳከብርህ አድርገኝ።
እግዚአብሔርን “አንተ መከታዬና መጠጊያዬ ነህ፤ አንተ የምተማመንብህ አምላኬ ነህ” ይለዋል።
የማንኛውም አገር ሰው ቢሆን እግዚአብሔርን የሚፈራና ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግ ከሆነ እግዚአብሔር ይቀበለዋል።