አምላክ ሆይ! ጩኸቴን አድምጥ፤ ጸሎቴንም ስማ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴን ስማ፤ ጸሎቴንም አድምጥ።
ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር።
ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን? መድኀኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።
እግዚአብሔር ሆይ! ልመናዬን ስማ! ምሕረትህን ፈልጌ ስጮኽም አድምጠኝ!
እግዚአብሔር ሆይ! ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርብልህን ጸሎት ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በሽንገላ ሳይሆን በእውነት የማቀርበውን ጸሎት ስማ።
ወደ ተቀደሰው ቤተ መቅደስህ እጄን አንሥቼ ለእርዳታ በምጮኽበት ጊዜ እባክህ ጸሎቴን ስማኝ።
አንተ የእውነት አምላክ ነህ፤ እባክህን ለጸሎቴ መልስ ስጠኝ! እኔ በጣም በጭንቀት ላይ ነበርኩ አንተ ግን ነጻ አወጣኸኝ፤ አሁንም ራራልኝና ጸሎቴን ስማ።
አምላክ ሆይ! በስምህ አድነኝ፤ በኀይልህም ፍረድልኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ።
አምላክ ሆይ! በችግሬ ምክንያት ወደ አንተ ስጸልይ ስማ፤ ከጠላት ማስፈራራትም ጠብቀኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ የልመናዬንም ጩኸት አድምጥ።
ስለዚህ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፥ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ።