መዝሙር 59:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላኬ በዘለዓለማዊ ፍቅሩ በፊቴ ይሄዳል፤ ጌታዬ፥ ጠላቶቼን በንቀት ዐይን እንድመለከታቸው ያደርገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በምሕረቱ ይገናኘኛል፤ አምላኬ የጠላቶቼን ውድቀት ያሳየኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነውና ኃይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላካችን ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም። |
ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ! በእነርሱ ላይ መቅሠፍትን እንድታመጣ ያሳሰብኩህ ጊዜ የለም፤ የመከራ ዘመን እንዲገጥማቸውም አልተመኘሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህንና የተናገርኩትን ሁሉ ታውቃለህ።
ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብር የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ እርሱ ራሱ ከተቀበላችሁት መከራ ያድናችኋል፤ ይደግፋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።
በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ራሱ ሳኦልን ይገድለዋል፤ የሚሞትበት ጊዜ ደርሶ፥ አለበለዚያም በጦርነት መሞቱ አይቀርም፤