Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 54:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ተንኰላቸውን በሚያስጨንቁኝ ጠላቶቼ ላይ መልስባቸው፤ እነርሱን በማጥፋት ታማኝነትህን አሳይ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የገዛ ክፋታቸው በሚያደቡብኝ ላይ ይመለስባቸው፤ በቃልህ ታማኝ ነህና አጥፋቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እንግዶች ተነሥተውብኛልና፥ ጨካኞችም ነፍሴን ሽተዋታልና። እግዚአብሔርን በፊታቸው አላደረጉትም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ፍር​ሃ​ትና እን​ቅ​ጥ​ቅጥ ያዙኝ፥ ጨለ​ማም ሸፈ​ነኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 54:5
11 Referencias Cruzadas  

ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ግለጥልኝ፤ ጠላቶቼን አጥፋቸው፤ እኔ አገልጋይህ ስለ ሆንኩ ጥቃት የሚያደርሱብኝን ሁሉ ደምስሳቸው።


ጌታ ሆይ! የቀድሞዎቹ የፍቅርህ ማረጋገጫዎች የት አሉ? ለዳዊት የሰጠኸውስ የተስፋ ቃል የት ነው?


እርሱ ስለ ክፋታቸው ይቀጣቸዋል፤ ስለ ኃጢአታቸውም ይደመስሳቸዋል፤ እግዚአብሔር አምላካችን ያጠፋቸዋል።


እናንተ ለእርሱ የተቀደሳችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን ውደዱት፤ እግዚአብሔር ታማኞችን ይጠብቃል፤ ለትዕቢተኞች ግን ተገቢ ቅጣታቸውን ይሰጣል።


እግዚአብሔር ሆይ! የምመራበትን መንገድ አስተምረኝ፤ በጠላቶቼም ምክንያት በተደላደለ መንገድ ምራኝ።


በሰጠችው መጠን ስጥዋት፤ ባደረገችውም ሥራ እጥፍ ክፈልዋት፤ እርስዋ ልዩ ልዩ መጠጦችን በቀላቀለችበት ጽዋ ውስጥ እጥፍ ኀይለኛ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤


የናስ አንጥረኛው እስክንድር ከፍተኛ ጒዳት አደረሰብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይከፍለዋል።


ባቢሎን ሆይ! አፍራሽዋ ባቢሎን! በእኛ ላይ ያደረግሽብንን የክፋት ብድራት ሁሉ በአንቺ ላይ የሚመልስብሽ የተባረከ ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! የሚጠባበቁኝ ጠላቶቼ ብዙዎች ናቸው! ስለዚህ ፈቃድህን እንዳደርግ ምራኝ፤ መንገድህንም በፊቴ አቅናልኝ።


እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ! ለምሕረት የማደርገውን ልመና አድምጥ! በታማኝነትህና በእውነተኛነትህ ለጸሎቴ መልስ ስጠኝ!


አምላክ ሆይ! ትዕቢተኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፤ አንተን የማይፈሩ ጨካኞች ሰዎች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios