መዝሙር 58:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ገዢዎች! በትክክል ትናገራላችሁን? በሰዎችስ መካከል ያለ አድልዎ ትፈርዳላችሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀያላን ሆይ፤ በውኑ ጽድቅ ከአፋችሁ ይወጣል? የሰው ልጆች ሆይ፤ በቅን ትፈርዳላችሁን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። የዳዊት ቅኔ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶች አድነኝ፤ በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ። |
እንግዲህ የእስራኤል መሪዎች ሁሉ በኬብሮን ወደ ነበረው ወደ ዳዊት የመጡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ እርሱም ከእነርሱ ጋር በእግዚአብሔር ፊት የቃል ኪዳን ስምምነት አደረገ፤ እነርሱም ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሕዝብ አመራር በመስጠት የታወቁ ሰባ ሽማግሌዎችን ምረጥ፤ እነርሱንም ሰብስበህ ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣቸውና በአጠገብህ ይቁሙ፤
ሐዋርያቱም ትእዛዙን ተቀብለው በማለዳ ወደ ቤተ መቅደስ ገቡና ማስተማር ጀመሩ። በዚያን ጊዜ የካህናት አለቃውና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጥተው የሸንጎውን አባሎችና የአይሁድ ሽማግሌዎችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰቡ፤ ሐዋርያትንም እንዲያመጡአቸው ሰዎችን ወደ ወህኒ ቤት ላኩ።