Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 58 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። የዳዊት ቅኔ።

2 በእውነት ጽድቅን ትናገራላችሁን፥ ገዢዎች ሆይ፥ በቅን ትፈርዳላችሁን?

3 በልባችሁ በምድር ላይ ግፍን ትሠራላችሁና፥ እጆቻችሁም ዐመጽን ይፈጽማሉና።

4 ክፉዎች ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፥ ከሆድም ጀምረው ሳቱ፥ ሐሰትንም ተናገሩ።

5 የእባብ መርዝ ዓይነት መርዝ አላቸው፥ ጆሮውን እንደደፈነ እባብ ናቸው፥

6 አስማተኛ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ።

7 አምላክ ሆይ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፥ የአንበሶቹን መንጋጋቸውን አድቅቅ።

8 እንደሚፈስስ ውኃ ይጥፉ፥ ቀስትን ሲገትሩ ፍላጻው ይጣመም።

9 እንደሚሟሟ ቀንድ አውጣ፥ ፀሐይን እንዳላየ ጭንጋፍ ይሁኑ።

10 ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።

11 ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፥ በክፉዉም ደም እግሮቹን ይታጠባል።

12 ሰውም፦ “በእውነት ለጻድቅ ፍሬ አለው፥ በእውነት በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ” ይላል።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos