መዝሙር 49:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ እንደ በጎች እንዲሞቱና እንዲቀበሩ ይደረጋሉ፤ እረኛ በጎችን እንደሚመራ ሞትም እነዚህን ወደ መቃብር ይመራል፤ ትክክለኞች ሰዎች በማለዳ በመቃብራቸው ላይ ይመላለሳሉ፤ ሥጋቸውም በመቃብር ውስጥ ይበሰብሳል፤ የሙታን ዓለምም መኖሪያቸው ይሆናል። ደጋግ ሰዎችም በማለዳ ተነሥተው በእነርሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ በጎች ለሲኦል የተዳረጉ ናቸው፤ ሞትም እረኛቸው ይሆናል፤ ቅኖች በማለዳ ይገዟቸዋል፤ አካላቸው ከክብር ቤታቸው ርቆ፣ በሲኦል ይፈራርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህች መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥ ከእነርሱም በኋላ የሚመጡ በንግግራቸው ይደሰታሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ጸሎትህን ስጥ፤ |
እግዚአብሔር ሆይ! እኔን ግን ታውቀኛለህ፤ ስለ አንተ ያለኝን አስተሳሰብ አይተህ ትፈትነኛለህ፤ እነዚህን ክፉ ሰዎች እንደሚታረዱ በጎች ውሰዳቸው፤ ለዕርድም ቀን ለይተህ አቈያቸው።
ይህም የሆነው ዘለዓለማዊው መጥቶ ለልዑል እግዚአብሔር ቅዱሳን ፍትሕ እስከ ሰጠበት ጊዜ ድረስ ነው፤ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወርሱበት ጊዜ ደረሰ።
ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”
የእግዚአብሔር ሰዎች በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን? ታዲያ፥ በዓለም ላይ የምትፈርዱ ሲሆን በዚህ በትንሽ ነገር ላይ መፍረድ ያቅታችኋልን?