ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ አዘጋጅቴ በራሳቸው ቦታ እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መሳፍንትን ከሾምኩበት ጊዜ ጀምሮ ክፉ አድራጊዎች ቀድሞ ያደርጉት እንደ ነበረው አያስጨንቋቸውም፤ አንተንም ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ከቤትህ አልጋህን የሚወርሱ ልጆች እተካልሃለሁ ብሎ ይገልጥልሃል።
መዝሙር 44:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጠላቶቻችን የምታድነን አንተ ነህ፤ የሚጠሉንንም የምታሳፍርልን አንተ ነህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ግን በጠላቶቻችን ላይ ድልን ትሰጠናለህ፤ ባላንጣዎቻችንንም ታሳፍራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀስቴ የምታመን አይደለሁምና፥ ሰይፌም አያድነኝምና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጽድቅን ወደድህ፥ ዐመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክህ የደስታ ዘይትን ቀባህ። |
ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ አዘጋጅቴ በራሳቸው ቦታ እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መሳፍንትን ከሾምኩበት ጊዜ ጀምሮ ክፉ አድራጊዎች ቀድሞ ያደርጉት እንደ ነበረው አያስጨንቋቸውም፤ አንተንም ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ከቤትህ አልጋህን የሚወርሱ ልጆች እተካልሃለሁ ብሎ ይገልጥልሃል።
ለይሁዳ ሕዝቦች ግን ፍቅር አሳያቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ፤ የማድናቸውም በጦርነት ኀይል አይደለም፤ በሰይፍ፥ በቀስትና በፍላጻ ወይም በፈረስና በፈረሰኛ አይደለም።”
አንተ ኢያሱ፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ አንተን ተቋቊሞ ድል የሚነሣህ ማንም አይኖርም፤ እኔ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር እሆናለሁ፤ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነኝ፤ ከቶም አልተውህም፤
ኢያሱ እነዚህን ነገሥታትና ግዛቶቻቸውን ሁሉ በአንድ ዘመቻ ድል ያደረገው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋላቸው ስለ ነበረ ነው።
እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራ፤ ስለ እስራኤል በመዋጋት ነገ ይህን ጊዜ ሁሉንም እንደ ሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ አንተም የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው።
እግዚአብሔር መስፍን ባስነሣላቸው ጊዜ ሁሉ እርሱ ከመስፍኑ ጋር ነበር፤ በሚያሳድዱአቸውና በሚጨቊኑአቸው ጠላቶች ምክንያት ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር በሚጮኹበት ጊዜ እግዚአብሔር ያዝንላቸው ስለ ነበረ በመስፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ ያድናቸው ነበር።
እዚህ የተሰበሰቡት ሁሉ እግዚአብሔር የሚያድነው በሰይፍና በጦር አለመሆኑን ያውቃሉ፤ ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነውና፤ በእናንተም ላይ ድልን እንድንጐናጸፍ ያደርገናል።”