መዝሙር 42:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ፤ ለምንስ እጨነቃለሁ። በእግዚአብሔር እተማመናለሁ። ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤ አዳኜና አምላኬን ገና አመሰግነዋለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፥ በዓል የሚያከብሩ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ። |
እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።
እናንተ ግን ደስ ይላችኋል፤ በተቀደሰ በዓል ምሽት እንደምትዘምሩት ትዘምራላችሁ፤ የእስራኤል አምባ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዋሽንት እየነፉ እንደሚዘምሩት ሰዎች ትደሰታላችሁ።
ከእናንተ መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራና ለአገልጋዩ ቃል የሚታዘዝ ማነው? ብርሃን የሌለው በጨለማ የሚመላለስ በእግዚአብሔር ይታመን፤ እምነቱንም በአምላኩ ላይ ይጣል።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።
ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤