መዝሙር 3:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ ሆይ! ተነሥ! አምላኬ ሆይ! መጥተህ አድነኝ! የጠላቶቼን መንጋጋ ስበር፤ ጥርሶቻቸውንም አድቅቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ! አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤ የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤ የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚከቡኝን አእላፍ ሕዝብ አልፈራም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤ አንተ በከንቱ የሚጠሉኝን ሁሉ መትተሃልና፥ የኃጥኣንንም ጥርስ ሰብረሃልና። |
እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።
እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።
ከእንጨት ተጠርቦ የተሠራውን ነገር “ንቃ!” ከድንጋይ ተቀርጾ የተሠራውንም ነገር “ተነሥ!” ለምትል ለአንተ ወዮልህ! ለመሆኑ ጣዖት አንዳች ምሥጢር ሊገልጥልህ ይችላልን? እነሆ ጣዖት በብርና በወርቅ ተለብጦ የተሠራ ነው፤ የሕይወት እስትንፋስ ግን ፈጽሞ የለውም።