መዝሙር 21:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ የሚተማመነው በእግዚአብሔር ነው፤ የማያቋርጠው የልዑል እግዚአብሔር ፍቅር ከእርሱ ጋር ስለ ሆነም አይናወጥም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ በእግዚአብሔር ተማምኗልና፤ ከልዑልም ጽኑ ፍቅር የተነሣ፣ ከቆመበት አይናወጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዘለዓለም በረከትን ሰጥተኸዋልና፥ በፊትህም ደስ ታሰኘዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያዩኝ ሁሉ ይጠቃቀሱብኛል፤ ራሳቸውን እየነቀነቁ በከንፈሮቻቸው እንዲህ ይላሉ፦ |
የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤ ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤ እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።
በልዩ ልዩ አገር የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ያገለግሉት ዘንድ ሥልጣን፥ ክብርና ንጉሥነት ተሰጠው፤ ግዛቱም የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።
ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤