በከበሮና በማሸብሸብ አመስግኑት፤ በክራርና በዋሽንት አመስግኑት።
በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤ በባለአውታር መሣሪያና በእንቢልታ አመስግኑት።
በከበሮና በሽብሸባ አወድሱት፥ በባለ አውታር መሣሪያና በእምቢልታ አወድሱት።
በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤ አውታር በአለው መሣሪያና በእንዚራ አመስግኑት።
አታሞ እየመቱ፥ በገና እየደረደሩ፥ እምቢልታ እየነፉ፥ በደስታ ይዘፍናሉ።
ደስታዬን እገልጥባቸው የነበሩት በገና እና እምቢልታ አሁን የሐዘን እንጒርጒሮዬ ማሰሚያ ሆነዋል።
አምላክ ሆይ! አዲስ መዝሙር እቀኝልሃለሁ፤ ዐሥር አውታር ያለው በገናም በመደርደር እዘምርልሃለሁ።
በማሸብሸብ ስሙን ያመስግኑት፤ ከበሮ እየመቱና በገና እየደረደሩ ያመስግኑት።
እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት።
ከከርቤ፥ ከእሬትና ከብርጒድ የተቀመመ ሽቶ በንጉሣዊ ልብስህ ላይ ተርከፍክፎአል፤ በዝሆን ጥርስ በተጌጠው ቤተ መንግሥትህም የበገና ሙዚቃ ቃና ያስደስትሃል።
ባለ አውታር በሆኑት የሙዚቃ መሣሪያዎችና በበገና ቅኝት አንተን ማመስገን እንዴት መልካም ነው?
የአሮን እኅት ነቢይቱ ማርያም ከበሮዋን አነሣች፤ ሌሎችም ሴቶች ከበሮዎቻቸውን እየመቱና እየጨፈሩ ይከተሉአት ጀመር፤
እግዚአብሔር ያድነኛል፤ ስለዚህ እኛ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ አውታር ባለው የሙዚቃ መሣሪያ የምሥጋና መዝሙር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዘምራለን።
ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴ ነው፤ እግሮቼንም እንደ ዋልያ እግሮች ያጠነክርልኛል፤ በተራሮችም ላይ እንድራመድ ያደርገኛል።