‘ወንድሞችህ በበደሉህ ጊዜ ያደረሱብህን ጒዳት ሁሉ አትቊጠርባቸው ብሎሃል’ ብለን እንድንነግርህ አዞናል፤ ስለዚህ እኛ የአባትህ አምላክ አገልጋዮች ያደረስንብህን በደል ሁሉ ይቅር እንድትለን እንለምንሃለን።” ዮሴፍ ይህን በሰማ ጊዜ አለቀሰ።
መዝሙር 146:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነለትና በአምላኩ በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረገ ሰው ደስ ይበለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብፁዕ ነው፤ ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣ ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በጌታ በአምላኩ የሆነ ሰው ምስጉን ነው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ ኀይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር የለውም። |
‘ወንድሞችህ በበደሉህ ጊዜ ያደረሱብህን ጒዳት ሁሉ አትቊጠርባቸው ብሎሃል’ ብለን እንድንነግርህ አዞናል፤ ስለዚህ እኛ የአባትህ አምላክ አገልጋዮች ያደረስንብህን በደል ሁሉ ይቅር እንድትለን እንለምንሃለን።” ዮሴፍ ይህን በሰማ ጊዜ አለቀሰ።
እኔ የቀድሞ አባቶችህ የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤” በዚህ ጊዜ ሙሴ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ።
እስራኤል ሆይ! የእርዳታህ ጋሻ፥ የድልህ ሰይፍ መዳንን ከእግዚአብሔር ያገኘ፥ እንዳንተ ያለ ሕዝብ ከቶ የለም፤ ምንኛ የታደልክ ነህ! ጠላቶች እየተለማመጡ ወደ አንተ ሲመጡ ጀርባቸውን ትረግጣለህ።
እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በኢየሱስ አማካይነት እርሱን ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ትተማመናላችሁ።