Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 146 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


የሐጌና የዘካርያስ መዝሙር።

1 ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን አመስግኚ።

2 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ጌታን አመሰግናለሁ፥ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።

3 ማዳን በማይችሉ በአለቆች፥ በሰው ልጅ፥ አትታመኑ።

4 ነፍሱ ትወጣለች ወደ መሬቱም ይመለሳል፥ ያንጊዜ እቅዶቹ በሙሉ ይጠፋሉ።

5 የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በጌታ በአምላኩ የሆነ ሰው ምስጉን ነው፥

6 እርሱም ሰማይንና ምድርን ባሕርንም፥ በእነርሱ ያለውንም ሁሉ የፈጠረ፥ እውነትን ለዘለዓለም የሚጠብቅ፥

7 ለተበደሉት የሚፈርድ፥ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ ነው። ጌታ የታሰሩትን ይፈታል፥

8 ጌታ የዕውሮችን ዐይን ያበራል፥ ጌታ የወደቁትን ያነሣል፥ ጌታ ጻድቃንን ይወድዳል፥

9 ጌታ ስደተኞችን ይጠብቃል፥ ወላጆች የሞቱባቸውንና ባልቴቶችን ይቀበላል፥ የክፉዎችንም መንገድ ያጠፋል።

10 ጌታ ለዘለዓለም ይነግሣል፥ ጽዮን ሆይ፥ አምላክሽ ለልጅ ልጅ ነው። ሃሌ ሉያ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos