መዝሙር 129:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከወጣትነቴ ጀምሮ አደጋ ደርሶብኛል፤ እስራኤላውያን እንዲህ ይበሉ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል እንዲህ ይበል፦ “ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዕርገት መዝሙር። እስራኤል፦ “ከትንሽነቴ ጀምሮ አብዝተው አጠቁኝ” ይበል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ። |
ከዚህ በኋላ በብርቱ ሥራ ይጨቊኑአቸው ዘንድ ጨካኞች የሆኑ አሠሪዎችን ሾሙባቸው፤ በዚህም ሁኔታ ዕቃ ማከማቻ የሆኑትን ፊቶምና ራምሴ የተባሉትን ከተሞች ለፈርዖን ሠሩ።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ “ከዕብራውያን የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ እያነሣችሁ ዓባይ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፤ ሴቶች ልጆች ግን በሕይወት ይኑሩ” ሲል ለሕዝቡ ጥብቅ ትእዛዝ አስተላለፈ።
እስኪ ከሆነልሽ ከሕፃንነትሽ ጊዜ ጀምሮ ስትጠቀሚባቸው የኖርሽውን ያፍዝ አደንግዝ ድግምትና የጥንቈላ መተቶችን አስቀምጪ፤ ምንአልባት ጥቂት ይረዳሽ ይሆናል፤ ወይም ጠላቶችሽን ልታስፈራሪባቸው ትችያለሽ፤
“ሂድና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በመጀመሪያ በምድረ በዳ ምንም በማያበቅልበት ትከተሉኝ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ሙሽራይቱ ለሙሽራው የምታሳየውን ፍቅርና ታማኝነት ለኔም ታሳይ እንደ ነበረ አስታውሳለሁ።
በብልጽግና በምትኖሩበት ጊዜ እግዚአብሔር ተናገራችሁ፤ እናንተ ግን ማዳመጥ እምቢ አላችሁ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ የምታደርጉት ይህንኑ ነው። እግዚአብሔርንም መታዘዝ እምቢ አላችሁ።
የይሁዳ ሕዝብ ከጭንቀትና ከከባድ የባርነት ሥራ በኋላ ወደ ምርኮ ተወሰዱ፤ አሁን እነርሱ በሕዝቦች መካከል ሲኖሩ ዕረፍት አያገኙም፤ እነርሱ በጭንቀት ውስጥ እያሉ አሳዳጆቻቸው ደረሱባቸው።
የቀድሞውን የወይን ተክል እመልስላታለሁ፤ የመከራንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ፤ እዚያም ከግብጽ ስትወጣ በወጣትነትዋ ወራት በነበራት ሁኔታ በደስታ ትዘምራለች።
ወደ ጦርነት በሄዱም ቊጥር ቀደም ብሎ በመሐላ በተናገረው መሠረት እግዚአብሔር ራሱ ይቃወማቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እነርሱ በብርቱ ጭንቀት ላይ ወደቁ።
ከዚህም የተነሣ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነደደ፤ ለመስጴጦምያው ንጉሥ ለኩሻን ፊሽዓታይም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለኩሻን ሪሽዓታይም ስምንት ዓመት ተገዙለት፤
ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ ፍልስጥኤማውያን ቊጥጥር ያደርጉባቸው ስለ ነበር በዚያን ዘመን በእስራኤል ብረት አቅልጠው የሚሠሩ ጠቢባን አልነበሩም፤