ስለዚህ በዚያን ምሽት አባታቸውን እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተው አሰከሩት፤ ታናሽቱ ልጁም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አደረገች፤ አሁንም እጅግ ሰክሮ ስለ ነበር ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።
ምሳሌ 24:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጻድቅ ሰው ሰባት ጊዜ ቢወድቅ እንኳ እንደ ገና ይነሣል፤ ዐመፀኞች ግን ጥፋት ይደርስባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቅ ሰባት ጊዜ እንኳ ቢወድቅ ይነሣልና፤ ክፉዎች ግን በጥፋት ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃልና፤ ደግሞም ይነሣል፥ ክፉዎችን ግን መጥፎ ነገር ሲገጥማቸው ይወድቃሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል፥ ሰባት ጊዜም ይነሣል። ኃጥኣን ግን በክፉ ደዌ ይያዛሉ። |
ስለዚህ በዚያን ምሽት አባታቸውን እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተው አሰከሩት፤ ታናሽቱ ልጁም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አደረገች፤ አሁንም እጅግ ሰክሮ ስለ ነበር ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።
ትቢያ በምሥራቅ ነፋስ እንደሚበተን፥ ሕዝቤን በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ። ፊቴን ከእነርሱ መልሼ ጀርባዬን እሰጣቸዋለሁ። ጥፋት በሚመጣባቸውም ጊዜ ፈጽሞ አልረዳቸውም።”
‘አሺማ’ ተብላ በምትጠራ በሰማርያ ሴት አምላክ የሚምሉ ‘በዳን አምላክ’ ወይም ‘በቤርሳቤህ አምላክ’ እያሉ የሚምሉ ሁሉ ይወድቃሉ፤ ከወደቁበትም ፈጽሞ መነሣት አይችሉም።”
ቃላችሁን ባትጠብቁ ግን እግዚአብሔርን የምታሳዝኑ ሆናችሁ እንዳትገኙ አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ሰለ ኃጢአታችሁም ቅጣት የሚደርስባችሁ መሆኑንም አትዘንጉ።
ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።
በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ራሱ ሳኦልን ይገድለዋል፤ የሚሞትበት ጊዜ ደርሶ፥ አለበለዚያም በጦርነት መሞቱ አይቀርም፤
ጋሻጃግሬው የነበረውንም ወጣት “እነዚህ ያልተገረዙ እኔን ወግተው በመሳለቅ መጫወቻ እንዳያደርጉኝ አንተ ራስህ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው፤ ወጣቱ ግን ፈርቶ አልገደለውም፤ ስለዚህም ሳኦል ራሱ የገዛ ሰይፉን ወስዶ በስለቱ ላይ ወደቀበት።