ምሳሌ 21:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን የልብን ሐሳብ ይመዝናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፥ ጌታ ግን ልብን ይመዝናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ሁሉ ለራሱ ጻድቅ መስሎ ይታያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያቀናል። |
ምናልባት “እኔ አላውቀውም” ትል ይሆናል፤ ነገር ግን ልብን የሚመረምር አያስተውለውምን? እርሱ ሕይወትህን የሚጠብቅ እርሱ አያውቀውምን? እያንዳንዱንስ እንደ ሥራው አይከፍለውምን?
እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ራሳችሁን በሰው ፊት ጻድቅ ታስመስላላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ፊት ክብር ያለው መስሎ የሚታይ፥ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው።”
ልጆችዋንም በሞት እቀጣለሁ፤ አብያተ ክርስቲያንም ሁሉ የሰውን ሐሳብና ምኞት የምመረምር እኔ መሆኔን ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደየሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።
እግዚአብሔር ግን “የኤሊአብን ቁመት መርዘምና መልከ ቀናነቱን አትይ፤ እኔ እርሱን አልፈለግሁትም፤ እኔ የምፈርደው ሰዎች እንደሚፈርዱት አይደለም፤ ሰው የውጪ መልክን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።