12 በጣም የረከሱ ሆነው ሳለ ንጹሕ የሆኑ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ።
12 ራሳቸውን ንጹሓን አድርገው የሚቈጥሩ፣ ሆኖም ከርኩሰታቸው ያልነጹ አሉ፤
12 ለራሱ ንጹሕ የሆነ የሚመስለው ከርኩሰቱ ግን ያልጠራ ትውልድ አለ።
አንተ ስትናገር ‘በደልና እንከን የሌለብኝ፥ ከኃጢአት ንጹሕ የሆንኩ፥ ነጻ ነኝ፤
ክፉ ሰው ክፋቱ ስለሚያቈላምጠው ኃጢአቱን ለማየትም ሆነ ለመጥላት አይፈልግም።
በደሌን ሁሉ አጥበህ አስወግድልኝ፤ ከኃጢአቴም አንጻኝ።
በሂሶጵ ቅጠል ረጭተህ ኃጢአቴን አስወግድልኝ፤ እኔም እነጻለሁ። እጠበኝ፤ እኔም ከበረዶ ይበልጥ ነጭ እሆናለሁ።
ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል የሆነ ሊመስለው ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ዓላማውን ይመዝናል።
ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን የልብን ሐሳብ ይመዝናል።
ይልቁንስ ታጥባችሁ ንጹሕ ሁኑ፤ ክፉ ሥራችሁን ሁሉ ከፊቴ አስወግዱ፤ በደል መፈጸማችሁንም ተዉ።
እነርሱ፥ ‘እኛ ቅዱሳን ስለ ሆንን ወደ እኛ አትቅረቡ!’ የሚሉ ናቸው፤ እነዚህ ነገሮች ቀኑን ሙሉ ለሚነድ እሳት ኀይለኛ ቊጣዬን የሚያቀጣጥሉ ናቸው።
“ኢየሩሳሌም ሆይ! መዳን ከፈለግሽ ክፋትን ሁሉ ከልብሽ አጥበሽ አስወግጂ፤ ለመሆኑ የኃጢአት ሐሳብ ከአእምሮሽ የማይጠፋው እስከ መቼ ነው?
በእናንተ ላይ ንጹሕ ውሃ በመርጨት ከጣዖት አምልኮአችሁና ከርኲሰታችሁ ሁሉ እንድትነጹ አደርጋለሁ።
ነገር ግን ከግብጽ ምድር መርቼ ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ በዳስ በዓል ጊዜ በድንኳን እንደምትኖሩ ዐይነት፥ እንደገና ተመልሳችሁ በድንኳን እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ለዳዊት ልጆችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአታቸውና ከርኲሰታቸው የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።
እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ራሳችሁን በሰው ፊት ጻድቅ ታስመስላላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ፊት ክብር ያለው መስሎ የሚታይ፥ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው።”
“ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ ሲል በልቡ ጸለየ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኔ እንደ ሌሎች ሰዎች ቀማኛ፥ ግፈኛ አመንዝራ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ፤ ይልቁንም እንደዚህ እንደ ቀራጭ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ።
ከእናንተም አንዳንዶቻችሁ እንዲሁ ነበራችሁ፤ አሁን ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላካችን መንፈስ ከኃጢአት ታጥባችኋል፤ ለእግዚአብሔር የተለየ ቅዱስ ሕዝብ ሆናችኋል፤ ጸድቃችኋልም።
እግዚአብሔርን የሚያመልኩ መስለው ይታያሉ፤ የአምልኮትን ኀይል ግን ይክዳሉ፤ እንደነዚህ ካሉት ሰዎች ራቅ።
እኛ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን ራሱ በምሕረቱ አዳነን፤ ያዳነንም በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በተገኘው መታደስ ነው።
ሚካም “እንግዲህ ሌዋዊ ካህን ካገኘሁ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር እንደሚያሳካልኝ ዐውቃለሁ” አለ።
ይህ ሚካ የተባለ ሰው የራሱ የሆነ የአምልኮ ስፍራ ነበረው፤ በርከት ያሉ ጣዖቶች አንድ ኤፉድ ሠርቶ ከልጆቹ አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው ሾመው፤