Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 16:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ራሳችሁን በሰው ፊት ጻድቅ ታስመስላላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ፊት ክብር ያለው መስሎ የሚታይ፥ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ በሰዎች ፊት ራሳችሁን የምታጸድቁ ናችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰዎች ዘንድ የከበረ፣ በእግዚአብሔር ፊት የረከሰ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እንዲህም አላቸው “ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኩሰት ነውና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ለሰው ይም​ሰል ትመ​ጻ​ደ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ች​ሁን ያው​ቃል፤ በሰው ዘንድ የከ​በረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ናቀ ይሆ​ና​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እንዲህም አላቸው፦ ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት ነውና።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 16:15
40 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ግን “የኤሊአብን ቁመት መርዘምና መልከ ቀናነቱን አትይ፤ እኔ እርሱን አልፈለግሁትም፤ እኔ የምፈርደው ሰዎች እንደሚፈርዱት አይደለም፤ ሰው የውጪ መልክን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።


ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን የልብን ሐሳብ ይመዝናል።


ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።


እኔ እግዚአብሔር ግን የሰውን አእምሮና የሰውን ልብ እመረምራለሁ፤ እያንዳንዱንም ሰው በአካሄዱና በሥራው መጠን ዋጋውን እሰጠዋለሁ።”


እግዚአብሔር ትምክሕተኞችን ሁሉ ይጸየፋል፤ ከቅጣት እንዲያመልጡም አያደርጋቸውም።


የሰውን ልብ የሚያውቅ አምላክ፥ መንፈስ ቅዱስን ለእኛ እንደ ሰጠው ዐይነት ለእነርሱም በመስጠት መሰከረላቸው።


ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጭምትነት መንፈስ ያጌጠው፥ በልብ ተሰውሮ የሚገኘው፥ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን።


ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ “እናንተ ፈሪሳውያን የብርጭቆውንና የሳሕኑን ውጪውን አጥርታችሁ ታጥባላችሁ፤ በውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶባችኋል።


አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤


የሕግ መምህሩ ግን ራሱን ጻድቅ ለማድረግ ፈልጎ፥ “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው።


ልጆችዋንም በሞት እቀጣለሁ፤ አብያተ ክርስቲያንም ሁሉ የሰውን ሐሳብና ምኞት የምመረምር እኔ መሆኔን ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደየሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


ስለዚህ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት፥ ሕግን በመፈጸም አይጸድቅም፤ ሕግ የሚያሳየው ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑን ነው።


እርሱ በሰው ልብ ያለውን ሁሉ ያውቅ ስለ ነበር ስለ ሰው ማንም እንዲነግረው አያስፈልገውም ነበር።


ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት ሰው እንዲያይላቸው ብለው ነው፤ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የጸሎት ልብሳቸውን ዘርፍ ያስረዝማሉ፤


ሰውየውም “እነዚህን ትእዛዞች ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ” አለው።


ሰው ሁሉ ስለ ራሱ ደግነት ያወራል፤ ነገር ግን በእውነት ታማኝ የሆነውን ሰው ማን ሊያገኝ ይችላል!


“ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ ሲል በልቡ ጸለየ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኔ እንደ ሌሎች ሰዎች ቀማኛ፥ ግፈኛ አመንዝራ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ፤ ይልቁንም እንደዚህ እንደ ቀራጭ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ።


ኅሊናንና ልብን የምትመረምር ጻድቅ አምላክ ሆይ! የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ የጻድቃንንም ደኅንነት ጠብቅ።


ጸሎታቸውን ስማ፤ በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን በመስማት በደላቸውን ይቅር በላቸው፤ በሰው ልብና አእምሮ ያለውን ሐሳብ ሁሉ መርምረህ የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ፤ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የሚገባውን ዋጋ ስጠው።


ነገር ግን ይህ ሰው በክፉ ሥራው ዋጋ መሬት ገዛ፤ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ተዘረገፈ፤


እነርሱም ለታይታ በሚያቀርቡት ረጅም ጸሎት እያመካኙ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች ይበዘብዛሉ፤ ስለዚህ እነርሱን የባሰ ፍርድ ያገኛቸዋል።”


ስለዚህ ኢየሱስን ለመያዝ ምቹ ጊዜ ይጠብቁ ነበር። ለገዥው ሥልጣንና ፍርድ አሳልፈው ለመስጠት የሚያስችላቸውን የወንጀል ቃል ከእርሱ ለማግኘት ይፈልጉ ነበር፤ ስለዚህ ቅን ሰዎች መስለው፥ በንግግሩ የሚያጠምዱትን ሰላዮች ላኩበት።


ኢየሱስም ቀጥሎ እንዲህ አለ፦ “በምትጾሙበት ጊዜ፥ መጾማቸውን ሰዎች እንዲያውቁላቸው፥ ፊታቸውን እንደሚለውጡት እንደ ግብዞች፥ ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ በእውነት እላችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


“በምትጸልዩበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ! እነርሱ ሰው እንዲያይላቸው ብለው በየምኲራቡና በየመንገዱ ዳር ቆመው መጸለይ ይወዳሉ። በእውነት እላችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን በቅድሚያ አግኝተዋል።


ስለዚህ ለድኾች ምጽዋት በምትመጸውትበት ጊዜ፥ ግብዞች በየምኲራቡና በየመንገዱ እንደሚያደርጉት ለታይታ አታድርጉ፤ በእውነት እነግራችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን አስቀድመው አግኝተዋል።


እንደምናየው ከሆነ እነሆ፥ ክፉ አድራጊዎች ዕድለኞች ናቸው፤ በእርግጥም እነርሱ በብልጽግና ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርን እንኳ እየተፈታተኑት ምንም ችግር አይደርስባቸውም እያላችሁ ትናገራላችሁ።’ ”


ሰው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ቢደሰትና ሁሉም ነገር ስለ ተሳካለት ቢመሰገንም እንኳ


ይህ በራሳቸው የሚተማመኑ የሞኞችና የእነርሱን አባባል የሚቀበሉ ሰዎች ዕድል ፈንታ ነው።


ሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፥ እኔ እንደምወድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “በጎቼን አሰማራ፤


ኃጢአተኛ በክፉ ምኞቱ ይመካል፤ ጌታ ሆይ! እነዚህ ስግብግብ ሰዎች ይጠሉሃል፤ ይሰድቡህማል።


ቀጥሎም ኢየሱስ ጻድቃን ነን እያሉ ለሚመኩና ሌሎችንም ለሚንቁ ሰዎች፥ ይህን ምሳሌ ተናገረ፤


ጽድቅን አግኝቶ ወደ ቤቱ የተመለሰው ይህ ቀራጭ ነው እንጂ ፈሪሳዊው አይደለም እላችኋለሁ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ግን ከፍ ይላል።”


እንዲህ ሲሉም ጸለዩ፦ “የሰውን ሁሉ ልብ የምታውቅ ጌታ ሆይ፥ ከነዚህ ከሁለቱ ማንን እንደ መረጥክ አሳየን፤


የሰውን ልብ የሚመረምር አምላክ የመንፈስ ቅዱስ ሐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፤ መንፈስ ቅዱስ ስለ ምእመናን የሚያማልደው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios