Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 24:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ምናልባት “እኔ አላውቀውም” ትል ይሆናል፤ ነገር ግን ልብን የሚመረምር አያስተውለውምን? እርሱ ሕይወትህን የሚጠብቅ እርሱ አያውቀውምን? እያንዳንዱንስ እንደ ሥራው አይከፍለውምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አንተም፣ “ስለዚህ ነገር ምንም አላውቅም” ብትል፣ ልብን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ሕይወትህን የሚጠብቃት እርሱ አያውቅምን? ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን አይከፍለውምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እነሆ፥ ይህን አላውቀውም ብትል፥ ልቦችን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ነፍስህንም የሚመለከት እርሱ አያውቅምን? ለሰውስ ሁሉ እንደ ሥራው አይመልስለትምን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እነሆ፥ ይህን አላውቅም ብትል፥ እግዚአብሔር የሁሉን ልብ እንዲያውቅ ዕወቅ። ለሁሉ እስትንፋስን የፈጠረ እርሱ ሁሉን ያውቃል። ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፍለዋል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 24:12
35 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ለሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል፤ በአካሄዱም መጠን የሚገባውን ያደርግለታል።


ልጆችዋንም በሞት እቀጣለሁ፤ አብያተ ክርስቲያንም ሁሉ የሰውን ሐሳብና ምኞት የምመረምር እኔ መሆኔን ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደየሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደየሥራው ይሰጠዋል።


ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን የልብን ሐሳብ ይመዝናል።


እኔ እግዚአብሔር ግን የሰውን አእምሮና የሰውን ልብ እመረምራለሁ፤ እያንዳንዱንም ሰው በአካሄዱና በሥራው መጠን ዋጋውን እሰጠዋለሁ።”


በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።


ከቤትህ ወጥተህ ስትሄድና ወደ ቤትህም ስትመለስ ዛሬም ለዘለዓለሙ ይጠብቅሃል።


ጠባቂህ ዘወትር ንቁ ስለ ሆነ እንድትሰናከል አያደርግህም።


እግዚአብሔር ግን “የኤሊአብን ቁመት መርዘምና መልከ ቀናነቱን አትይ፤ እኔ እርሱን አልፈለግሁትም፤ እኔ የምፈርደው ሰዎች እንደሚፈርዱት አይደለም፤ ሰው የውጪ መልክን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።


ጌታ ሆይ! ለሁሉም እንደየሥራው ስለምትከፍል ዘለዓለማዊ ፍቅር ያንተ ነው።


ልቤን ብትመረምር፥ በሌሊት ብትጐበኘኝ፥ ብትፈትነኝም፥ ከእኔ ክፋትን አታገኝም፤ አንደበቴም አይስትም።


“እነሆ! እኔ በቶሎ እመጣለሁ! ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምሰጠውን ዋጋ ይዤአለሁ፤


“ለትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ የእሳት ነበልባል የሚመስሉ ዐይኖች ካሉትና በእሳት ፍም የነጠረ ናስ የሚመስሉ እግሮች ካሉት፥ ከእግዚአብሔር ልጅ የተነገረ ነው፤


እኔም ሕያው ነኝ፤ ሞቼ ነበር፤ ነገር ግን እነሆ፥ ለዘለዓለም ሕያው ነኝ፤ በሞትና በሲኦል ላይ ሥልጣን አለኝ።


እያንዳንዱ በምድራዊ ሕይወቱ ላደረገው ክፉም ሆነ ደግ ነገር እንደየሥራው ዋጋውን ለመቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረብ አለብን።


ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።


ይህም የሚሆነው እኔ በማበሥረው የወንጌል ቃል መሠረት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰዎች በሠሩት ስውር ነገር ላይ በሚፈርድበት ቀን ነው።


‘ሕይወት የምናገኘውና የምንንቀሳቀሰው፥ የምንኖረውም በእርሱ ነው፤’ ይህም የእናንተ ባለ ቅኔዎች ‘እኛ ሁላችን የእርሱ ልጆች ነን’ እንዳሉት ነው።


የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ሆኖ ከመላእክቱ ጋር ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይከፍለዋል።


ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ ከቤተ መቅደሱ ተዘርፈው የመጡትን የወርቅ ዕቃዎች አስመጥተህ አንተና መኳንንቶችህ፥ ሚስቶችህና ቁባቶችህ የወይን ጠጅ መጠጫ አደረጋችኋቸው፤ ከጠጣችሁም በኋላ ማየት ወይም መስማት የማይችሉትንና ምንም ነገር የማያውቁትን ከወርቅ፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከብረት፥ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት አመሰገናችሁ፤ መግደል ወይም ማዳን የሚችለውንና አካሄድህን የሚቈጣጠረውን ሕያው አምላክ ግን አላከበርከውም።


ዓላማህ ታላቅ ነው፤ ሥራህም ኀያል ነው፤ ሕዝቦች የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ ታያለህ፤ ለእያንዳንዱም ሰው እንደአካሄዱና እንደየሥራው ዋጋውን ትከፍላለህ።


እግዚአብሔር ሰው የሚያደርገውን ሁሉ ያያል፤ የሚሄድበትንም መንገድ ሁሉ ይመለከታል።


እርሱ በሕይወት ጠብቆናል፤ እንድንወድቅም አላደረገም።


አንተ የተሰወረውን ሐሳባችንን ስለምታውቅ በደላችንን ገልጠህ ባየህብን ነበር።


ኅሊናንና ልብን የምትመረምር ጻድቅ አምላክ ሆይ! የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ የጻድቃንንም ደኅንነት ጠብቅ።


ማንም ሰው በአንተ ላይ አደጋ ጥሎ ሊገድልህ ቢፈልግ አንድ ሰው ውድ የሆነ ሀብቱን እንደሚጠብቅ አምላክህ እግዚአብሔር አንተን በሰላም ይጠብቅሃል፤ ስለ ጠላቶችህም የሆነ እንደ ሆነ አንድ ሰው ድንጋዩን ከወንጭፍ እንደሚያስፈነጥር እግዚአብሔር ራሱ አሽቀንጥሮ ይጥላቸዋል።


እግዚአብሔር ይገድላል፤ ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፤ ከሲኦልም ያወጣል፤


እስቲ በመታበይ አትጓደዱ፤ የትምክሕት ንግግራችሁንም አስወግዱ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሁሉን ያውቃል፤ ሕዝብ የሚሠራውንም ሁሉ በፍርድ ይመዝናል።


ጆሮን የፈጠረ አምላክ አይሰማምን? ዐይንንስ የፈጠረ አምላክ አያይምን?


የምታገኘው በረከት የመልካም ንግግርህና ሥራህ ውጤት ነው፤ በዚህ ዐይነት ተገቢ ዋጋህን ታገኛለህ።


ኃጢአተኛን ሰው የገዛ ራሱ ክፋት ያጠምደዋል፤ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።


ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል የሆነ ሊመስለው ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ዓላማውን ይመዝናል።


የአንድ ሰው ጉዳይ ፍትሕ በሚያጣበት ጊዜ በውኑ ጌታ እነዚህን ነገሮች አያይምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios