ዘኍል 6:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሮንና ልጆቹ የእስራኤልን ሕዝብ በሚባርኩበት ጊዜ እንዲህ በሉ ብለህ ንገራቸው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሮንንና ልጆቹን እንዲህ በላቸው፤ ‘እስራኤላውያንን በምትባርኩበት ጊዜ እንዲህ በሏቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ ብለህ ተናገር፦ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፤ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፦ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦ |
ስለዚህ በዚያን ቀን እንዲህ ሲል ባረካቸው፤ “እስራኤላውያን በሚመርቁበት ጊዜ የእናንተን ስም በማስታወስ፥ ‘እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርጋችሁ’ ይላሉ።” በዚህ አኳኋን ያዕቆብ ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው።
የቀዓት የበኲር ልጅ ዓምራም፥ የአሮንና የሙሴ አባት ነበር፤ አሮንና ዘሮቹ ለዘለቄታው ለንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች እንዲሆኑ፥ እግዚአብሔርን በማምለክ ሥነ ሥርዓት ላይ ዕጣን እንዲያጥኑ፥ እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉና በስሙም ሕዝቡን እንዲባርኩ ተለይተው ነበር፤
ካህናቱና ሌዋውያኑም ቆመው የእግዚአብሔር በረከት በሕዝቡ ላይ እንዲወርድ ጸለዩ፤ እግዚአብሔርም በተቀደሰ መኖሪያው በሰማይ ሆኖ ጸሎታቸውን ሰማ።
ስለዚህ በሮም ለምትኖሩ፥ እግዚአብሔር ለወደዳችሁና ወገኖቹ እንድትሆኑ ለጠራችሁ ሁሉ፦ ከአባታችን ከእግዚአብሔርና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
በዚያን ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከሙ፥ በፊቱም በመቆም እንዲያገለግሉትና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ የሌዊን ነገድ በመለየት ሾመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሌዊ ነገድ ትውልድ አገልግሎት ይኸው ነው።
እርሱን እንዲያገለግሉት፥ በእርሱ ስም እንዲባርኩ፥ የክርክርና የወንጀል ጉዳይ በእነርሱ እንዲወሰን አምላክህ እግዚአብሔር ካህናቱን የሌዊን ልጆች ስለ መረጣቸው ወደ አስከሬኑ ይቅረቡ።
መልከጼዴቅ የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበር፤ ይህ መልከጼዴቅ አብርሃም ነገሥታትን አሸንፎ ሲመለስ በመንገድ ተገናኝቶ ባረከው።
የእስራኤልን ሕዝብ እንዲባርኩ ቀደም ብሎ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እስራኤላውያን ሁሉና መጻተኞች ሽማግሌዎቻቸው፥ ሹሞቻቸውና ዳኞቻቸው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከተሸከሙት ከሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት ግራና ቀኝ እኩሌቶቹ ከጌሪዚም ተራራ ፊት ለፊት፥ እኩሌቶቹ ደግሞ ከኤባል ተራራ ፊት ለፊት ቆሙ።
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ በዐቀደው መሠረት ለተመረጣችሁት፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመታዘዝና በደሙ ተረጭታችሁ ለመንጻት በመንፈስ ቅዱስ ለተቀደሳችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።