Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 47:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን ወደ ፈርዖን አቀረበው፤ ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን ቤተ መንግሥት አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቀረበው፤ ያዕቆብም ፈርዖንን ከመረቀው በኋላ

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው፥ ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ዮሴ​ፍም ያዕ​ቆ​ብን አባ​ቱን አስ​ገ​ብቶ በፈ​ር​ዖን ፊት አቆ​መው፤ ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 47:7
18 Referencias Cruzadas  

እንዲህ ብሎም አብራምን ባረከው፤ “ሰማይንና ምድርን የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ!


ያዕቆብ በኬብሮን አጠገብ መምሬ ወደምትባል ስፍራ ወደሚኖረው አባቱ ወደ ይስሐቅ ሄደ፤ ይህም ስፍራ አብርሃምና ይስሐቅ የኖሩበት ነው።


ያዕቆብ ፈርዖንን ባረከውና ተሰናብቶት ወጣ።


ፈርዖንም “ዕድሜህ ስንት ነው?” በማለት ያዕቆብን ጠየቀው።


ኢዮአብም በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት በአክብሮት ንጉሡን አመሰገነ፤ “የፈለግኹትን እንዳደርግ በመፍቀድህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አሁን ተረዳሁ” አለ።


ከዚህ በኋላ ዳዊትና ተከታዮቹ ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገሩ፤ ዳዊትም ባርዚላይን ሳመውና ባረከው፤ ባርዚላይም ወደ ቤቱ ተመልሶ ሄደ።


ስለዚህም ንጉሥ ሀዳድዔዜርን ድል በመንሣቱ ሰላምታና የደስታ መግለጫ ያቀርብለት ዘንድ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ ቀደም ሲልም ቶዒ በሀዳድዔዜር ላይ ጦርነት ሲያካሄድ የነበረ ነው፤ ዮራምም ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ የተሠሩ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ለዳዊት ይዞለት ሄደ።


ከዚህም በላይ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ባለሟሎች ሁሉ ወደ ንጉሥ ዳዊት ቀርበው ‘አምላክህ እግዚአብሔር ሰሎሞንን ከአንተ ይበልጥ ዝናው የገነነ፥ መንግሥቱንም ይበልጥ ታላቅ ያድርገው!’ ሲሉ አክብሮታቸውን ገልጠዋል፤ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት በአልጋው ላይ ሳለ ለእግዚአብሔር ሰገደ።


በሚቀጥለው ቀን ሰሎሞን ሕዝቡን ሁሉ አሰናበተ፤ ሁሉም ሰሎሞንን መረቁ፤ እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ስለ አደረገው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ብሎአቸው ወደየቤታቸው ሄዱ።


ኤልሳዕም ወደ ግያዝ መለስ ብሎ “በፍጥነት ተነሥና የእኔን ምርኲዝ ይዘህ ሂድ! ለአንድም ሰው ሰላምታ ለመስጠት እንኳ በመንገድ አትቁም፤ ማንም ሰው ሰላምታ ቢሰጥህ አጸፋውን ለመመለስ ጊዜ አታጥፋ፤ በቀጥታ ወደ ቤት ሄደህ የእኔን ምርኲዝ በልጁ ፊት ላይ አኑር!” አለው።


የበግ፥ የፍየልና የቀንድ ከብት መንጋችሁን ሁሉ ይዛችሁ ሂዱ፤ እኔንም ባርኩኝ።”


ሲበሉም ኢየሱስ ኅብስት አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ “እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው” ብሎ ሰጣቸው።


ቀጥሎም ኢየሱስ ኅብስት አንሥቶ ከአመሰገነ በኋላ፤ ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ “እንካችሁ፤ ይህ ለእናንተ የሚሰጥ ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” ብሎ ሰጣቸው።


ኢያሱም የይፉኔን ልጅ ካሌብን ባረከው፤ ኬብሮንንም ርስት አድርጎ ሰጠው፤


ኢያሱም ባርኮ አሰናበታቸውና ወደ ሰፈራቸው ሄዱ፤


ሰውን ሁሉ አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


ዔሊም ሕልቃናን ከሚስቱ ከሐና ጋር በሚመርቅበት ጊዜ፥ ሕልቃናን “ለእግዚአብሔር የተለየ አድርጋችሁ በሰጣችሁት በዚህ ልጅ ፈንታ ከዚህቹ ሴት ሌሎችን ልጆች ይስጥህ!” ይለው ነበር። ከዚያን በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos