ዘኍል 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክህነቱንም ሥራ ያከናውኑ ዘንድ አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፤ ከእነርሱ በቀር ሌላ ሰው ይህን ሥራ ለማከናወን ቢሞክር በሞት ይቀጣ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፤ እነርሱም ክህነታቸውን ይጠብቁ፤ ሌላ ሰው ማደሪያውን ቢቀርብ ግን ይገደል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፥ ክህነታቸውንም ይጠብቁ፤ ማናቸውም ሌላ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንንና ልጆቹን በምስክሩ ድንኳን ፊት አቁማቸው፤ ክህነታቸውንም፥ በመሠዊያውና በመጋረጃው ውስጥ ያለውንም ሁሉ ይጠብቁ፤ ከሌላ ወገን የዳሰሰ ቢኖር ይገደል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንንና ልጆቹን አቁማቸው፥ ክህነታቸውንም ይጠብቁ፤ ሌላ ሰውም ቢቀርብ ይገደል። |
እንዲሁም ኢዮርብዓም በኮረብታዎች ላይ የማምለኪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ የሌዊ ነገድ ካልሆኑ ቤተሰቦች መካከል ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ሾመ።
ንጉሥ ሰሎሞን በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ከመሥራቱ በፊት እግዚአብሔር በሚመለክበት ድንኳን የመዘመር ተግባራቸውን ያከናውኑ ነበር፤ የሥራቸውንም ቅደም ተከተል በተዘጋጀላቸው ተራ መሠረት ይፈጽሙ ነበር።
እኔ ግን “እንደ እኔ ያለ ሰው ሸሽቶ አይደበቅም፤ እንደ እኔ ያለ ሰው ሕይወቱን ለማዳን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት አለበትን? ይህን ከቶ አላደርገውም” ስል መለስኩለት።
ለወገባቸውም መታጠቂያ አድርግላቸው፤ በራሳቸውም ላይ ቆብ ድፋላቸው፤ ክህነታቸው ለዘለዓለም ቋሚ ሥርዓት ይሆናል፤ በዚህም ዐይነት አሮንንና ልጆቹን ትሾማለህ።
“ከተቀደሰው ስጦታ መብላት የሚችለው የካህን ቤተሰብ የሆነ ሰው ብቻ ነው፤ ሌላ ሰው ግን ከእርሱ አይብላ፤ ከካህኑ ጋር በእንግድነት ወይም ተቀጥሮ የሚኖር አይብላ።
ሰፈራችሁን ለቃችሁ በምትሄዱበት ጊዜ ሌዋውያን ብቻ ድንኳኑን ነቅለው በሚሰፍሩበት አዲስ ቦታ ይተክሉታል፤ ከእነርሱ በቀር ወደ ድንኳኑ የሚቀርብ ማንኛውም ሰው በሞት ይቀጣል።
ይህም ሁኔታ የአሮን ዘር ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር ዕጣን ያጥን ዘንድ ወደ መሠዊያው መቅረብ እንደማይገባው ለእስራኤላውያን ሁሉ ማስጠንቀቂያ ይሆናል፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዲህ የሚያደርግ ሰው ሁሉ እንደ ቆሬና እንደ ተከታዮቹ ይጠፋል፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር።
እነርሱም እናንተን የመርዳት ተግባራቸውን እያከናወኑ ድንኳኑንም የመንከባከብ ኀላፊነት ይወስዳሉ፤ ይሁን እንጂ በተቀደሰው ስፍራና በመሠዊያው ላይ ያሉትን ንዋያተ ቅድሳት መንካት አይኖርባቸውም፤ ነክተው ቢገኙ ግን እነርሱም እናንተም በአንድነት ትሞታላችሁ።
ነገር ግን መሠዊያውንና ከመጋረጃው በስተውስጥ በኩል ያለውን ቅድስተ ቅዱሳኑን የሚመለከተውን የክህነት አገልግሎት የምትፈጽሙ አንተና ልጆችህ ብቻ ናችሁ፤ የክህነትን አገልግሎት ዕድል ፈንታ አድርጌ ስለ ሰጠኋችሁ ይህ ሁሉ ኀላፊነት የእናንተ ነው፤ ካህን ያልሆነ ማንኛውም ሰው ወደዚያ ቢቀርብ ይሞታል።”
በመገናኛው ድንኳን በስተምሥራቅ፥ በፀሐይ መውጫ በኩል የሚሰፍሩት ሙሴ አሮንና የአሮን ልጆች ነበሩ፤ በመቅደሱ ውስጥ ስለ እስራኤል ሕዝብ ለሚፈጸም ማንኛውም ዐይነት የአገልግሎት ሥነ ሥርዓት ኀላፊዎች እነርሱ ነበሩ፤ ማንም ሌላ ሰው ወደ መቅደሱ ቢቀርብ በሞት ይቀጣል።
ስለዚህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር የአንድ አገር ዜጎችና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ናችሁ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።
ይህ ሚካ የተባለ ሰው የራሱ የሆነ የአምልኮ ስፍራ ነበረው፤ በርከት ያሉ ጣዖቶች አንድ ኤፉድ ሠርቶ ከልጆቹ አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው ሾመው፤
የታቦቱን ውስጣዊ ክፍል በመመልከታቸው እግዚአብሔር ተቈጥቶ ከቤት ሼሜሽ ሰዎች መካከል ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ይህን ሁሉ እልቂት በመካከላቸው በማድረጉ የቤት ሼሜስ ሰዎች በማዘን አለቀሱ።