Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከእስራኤላውያን ሁሉ ተለይተው ለአሮንና ለልጆቹ ያገለግሉ ዘንድ ሌዋውያንን መድባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሌዋውያኑን ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ፤ እነርሱም ከእስራኤላውያን ተለይተው ለርሱ ፈጽመው የተሰጡ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሌዋውያንንም ለአሮንና ለልጆቹ ትሰጣለህ፤ ከእስራኤል ልጆች መካከል ለእርሱ ፈጽሞ የተሰጡ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ አሮ​ንና ወደ ልጆቹ ወደ ካህ​ናቱ ታገ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ። ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተለ​ይ​ተው ለእኔ ሀብት ሆነው ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሌዋውያንንም ለአሮንና ለልጆቹ ትሰጣለህ፤ ከእስራኤል ልጆች ለእርሱ ፈጽመው ተሰጡ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 3:9
15 Referencias Cruzadas  

ከዚህም በኋላ ዳዊት እግዚአብሔር ለዘለዓለም እርሱን እንዲያገለግሉና የቃል ኪዳኑንም ታቦት እንዲሸከሙ የመረጣቸው እነርሱን ስለ ሆነ “የቃል ኪዳኑን ታቦት መሸከም የሚገባቸው ሌዋውያን ብቻ ናቸው” አለ።


በዚህ ቦታ ተመድበው የሚያገለግሉት ሰዎች የቤተሰብ የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው፦ የቀዓት ጐሣ፦ የመጀመሪያው የመዘምራን ቡድን መሪ ኢዩኤል ልጅ ዘማሪው ሄማን ነበር፤ የእርሱም የቤተሰብ የትውልድ ሐረግ ከዚህ በታች በተመለከተው አኳኋን እስከ ያዕቆብ ይደርሳል፦ ሄማን፥ ዮኤል፥ ሳሙኤል፥


ለቤተ መቅደስ ሥራ ከተመደቡትም መካከል ከምርኮ የተመለሱት ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ጺሐ፥ ሐሱፋ፥ ጣባዖት፥ ቄሮስ፥ ሲዓሃ፥ ፋዶን፥ ለባና፥ ሐጋባ፥ ዓቁብ፥ ሐጋብ፥ ሻምላይ፥ ሐናን፥ ጊዴል፥ ጋሐር፥ ረአያ፥ ረጺን፥ ነቆዳ፥ ጋዛም፥ ዑዛ፥ ፓሴሐ፥ ቤሳይ፥ አስና፥ መዑኒም፥ ነፊሲም፥ ባቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥ ባጽሉት፥ መሒዳ፥ ሐርሻ፥ ባርቆስ፥ ሲሣራ ቴማሕ፥ ነጺሐና ሐጢፋ።


በሙሴ መጽሐፍ በተጻፈውም መመሪያ መሠረት በኢየሩሳሌም ለተሠራው ቤተ መቅደስ አገልግሎት፥ ካህናቱን በየክፍላቸው፥ ሌዋውያኑን በየቡድናቸው አደራጁ።


በተጨማሪም የቀድሞ አባቶቻቸው ሌዋውያንን ይረዱ ዘንድ በንጉሥ ዳዊትና በባለሟሎቹ ተሹመው የነበሩ ብዛታቸው ሁለት መቶ ኻያ የሆነ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ነበሩ፤ እነርሱም በየስማቸው ተመዝግበዋል።


ወደ እርሱ ቀርባችሁ በማደሪያው ድንኳን አገልግሎታችሁን እንድትፈጽሙና በፊታቸውም ቆማችሁ የእስራኤልን ጉባኤ እንድታገለግሉ የእስራኤል አምላክ ከሌላው የእስራኤል ማኅበር መካከል መርጦ እናንተ የተለያችሁ እንድትሆኑ ማድረጉን እንደ ቀላል ነገር ታዩታላችሁን?


አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት በምታገለግሉበት ጊዜ ከእናንተ ጋር በመሥራት ይረዱአችሁ ዘንድ፥ የሌዊ ነገድ የሆኑትን ወገኖችህን ውሰድ፤


በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚገኙ መገልገያ ዕቃዎች ኀላፊዎች ይሆናሉ። እስራኤላውያንንም በድንኳኑ ውስጥ በማገልገል ተግባራቸውን ይፈጽማሉ።


በዚህም ዐይነት ሌዋውያን የኔ ይሆኑ ዘንድ ከቀሩት የእስራኤል ሕዝብ መካከል ለይልኝ፤


እኔ እነርሱን በኲር ሆነው ለሚወለዱት ለእስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ሁሉ ምትክ አድርጌ ስለ መረጥኳቸው የእኔ ብቻ ይሆናሉ።


እነሆ፥ አሁን ግን ስለ እስራኤላውያን በኲር ልጆች ምትክ ሌዋውያንን ለይቻለሁ፤


የእስራኤልን ሕዝብ ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲያገለግሉና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ በመቅረብ እንዳይቀሠፉ ይጠብቁአቸው ዘንድ፥ ሌዋውያንን ከእስራኤላውያን እንደ ስጦታ ተቀብዬ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻለሁ።”


እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ አንዳንዶቹ ነቢያት፥ አንዳንዶቹ የወንጌል ሰባኪዎች፥ አንዳንዶቹ የምእመናን እረኞች፥ አንዳንዶቹ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ስጦታዎችን ሰጣቸው።


ይህም፦ “ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ብዙ ምርኮኞችን ይዞ ሄደ፤ ለሰዎችም ስጦታዎችን ሰጠ” እንደ ተባለው ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos