Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 17:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ይህ ሚካ የተባለ ሰው የራሱ የሆነ የአምልኮ ስፍራ ነበረው፤ በርከት ያሉ ጣዖቶች አንድ ኤፉድ ሠርቶ ከልጆቹ አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው ሾመው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሚካ የተባለው ይህ ሰው የአምልኮ ስፍራ ነበረው፤ አንድ ኤፉድና ተራፊም ሠርቶ ከልጆቹ አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሚካ የተባለው ይህ ሰው የአምልኮ ስፍራ ነበረው፤ አንድ ኤፉድና ተራፊም ሠርቶ ከልጆቹ አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሰው​ዬ​ውም ሚካ የአ​ማ​ል​ክት ቤት ነበ​ረው፤ ኤፉ​ድና ተራ​ፊም አደ​ረገ፤ ከል​ጆ​ቹም አን​ዱን ቀደ​ሰው፤ ካህ​ንም ሆነ​ለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሰውዮውም ሚካ የአምላክ ቤት ነበረው፥ ኤፉድና ተራፊም አደረገ፥ ከልጆቹም አንዱን ቀደሰው፥ ካህንም ሆነለት።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 17:5
24 Referencias Cruzadas  

ላባ በጎች ሊሸልት ሄዶ ስለ ነበር፥ እርሱ በሌለበት ራሔል በቤት የነበሩትን የአባቷን ጣዖቶች ሰርቃ ሄደች።


ወደ ትውልድ አገርህ ለመመለስ ባለህ ብርቱ ፍላጎት እንደ ተለየኸኝ ዐውቃለሁ፤ ታዲያ የቤቴን ጣዖቶች የሰረቅህብኝ ለምንድን ነው?”


እንዲሁም ኢዮርብዓም በኮረብታዎች ላይ የማምለኪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ የሌዊ ነገድ ካልሆኑ ቤተሰቦች መካከል ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ሾመ።


ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዐይነት ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራቸውም ምስሎች በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃ ምስሉ መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም በቤትኤል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ፤


ከዚህም በቀር ቂሮስ ቀድሞ ንጉሥ ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ዘርፎ በመውሰድ በአማልክቱ ቤተ መቅደስ ያኖራቸውን እንደ ጽዋ ያሉትን ንዋያተ ቅድሳት መልሶ ሰጣቸው።


የሚቃጠል መሥዋዕት ወስደው ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡ ወጣቶች ወንዶችን ላከ፤ እነርሱም ወይፈኖችን የአንድነት መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።


“የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚጠየቅበትን የደረት ኪስ ለሊቀ ካህናቱ ሥራ፤ አሠራሩ እንደ ኤፉድ ሆኖ በተመሳሳይ ጥልፍ ያጌጠ ይሁን።


በዐይነት የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ የደረት ኪስ፥ ኤፉድ፥ ቀሚስ፥ በጥልፍ ያጌጠ ሸሚዝ፥ ጥምጥምና መታጠቂያ፤ ወንድምህ አሮንና ልጆቹ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ እነዚህን የተቀደሱ ልብሶች ይሥሩላቸው።


ለወገባቸውም መታጠቂያ አድርግላቸው፤ በራሳቸውም ላይ ቆብ ድፋላቸው፤ ክህነታቸው ለዘለዓለም ቋሚ ሥርዓት ይሆናል፤ በዚህም ዐይነት አሮንንና ልጆቹን ትሾማለህ።


አናጢ በእንጨቱ ላይ መስመርን ያሰምራል፤ ንድፍም ይነድፋል፤ በመላጊያ ያለሰልሰዋል፤ በማስተካከያ መሣሪያም ትክክልነቱን ያረጋግጣል፤ ውበት ያለው የሰው ቅርጽ እንዲኖረው ያደርጋል። ከዚያም በጣዖት ቤት ያኖረዋል።


የባቢሎን ንጉሥ በመስቀለኛ መንገዶቹ መታጠፊያ አጠገብ ይቆማል፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለበት ለማወቅ ፍላጻዎችን ይወረውራል፤ ጣዖቶቹንም ምክር ይጠይቃል፤ ለመሥዋዕት ከታረደ እንስሳ የጒበት ሞራ ወስዶም ይመረምራል።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ የራስ ዘውድህን አንሣ! ጥምጥምህን አውልቅ! ነገሮች እንደ ነበሩ አይቀሩም፤ ዝቅተኞችን በሥልጣን ከፍ አድርገህ አሁን ገዢዎች የሆኑትን ዝቅ አድርጋቸው!


በዚሁ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ ወይም ያለ መሪ፥ ያለ መሥዋዕት ወይም ያለ ሐውልት፥ ያለ ልብሰ ተክህኖ ወይም የጣዖት ምስል ለብዙ ዘመን ይኖራሉ፤


“የእስራኤል ሕዝብ ለራሳቸው ታላላቅ ቤተ መንግሥቶች ሠርተዋል፤ እኔን ፈጣሪአቸውን ግን ረስተዋል፤ የይሁዳም ሕዝብ ብዙ የተመሸጉ ከተሞችን ሠርተዋል፤ ስለዚህ ከተሞቻቸውንና ምሽጎቻቸውን የሚያቃጥል እሳት እልክባቸዋለሁ።”


የክህነቱንም ሥራ ያከናውኑ ዘንድ አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፤ ከእነርሱ በቀር ሌላ ሰው ይህን ሥራ ለማከናወን ቢሞክር በሞት ይቀጣ።”


እንደ አሮን በእግዚአብሔር የተጠራ ካልሆነ በቀር ማንም ይህን ክብር በገዛ ራሱ አያገኝም።


ልጁም ብሩን ለእናቱ ሰጣት፤ እርስዋም ከላዩ ሁለት መቶ ብር አንሥታ እንጨት ጠርቦ በብሩ በመለበጥ ጣዖት ለሚሠራላት የብር አንጥረኛ ሰጠችው፤ ጣዖቱም በሚካ ቤት ተቀመጠ።


በላዪሽ ዙሪያ ያለውን አገር ሊያጠኑ ተልከው የነበሩት አምስት ሰዎች ለጓደኞቻቸው “በዚህ ስፍራ ከነዚህ ቤቶች በአንዱ ውስጥ በብር የተለበጠ የእንጨት ጣዖት እንዳለ ታውቃላችሁን? ሌሎች ጣዖቶች አንድ ኤፉድም በተጨማሪ አለ፤ ታዲያ ምን ማድረግ የሚገባን ይመስላችኋል?” አሉአቸው።


ሚካም “እንዴት ‘ምን ሆነሃል’ ትሉኛላችሁ? የሚያገለግለኝን ካህንና እኔ የሠራኋቸውን ጣዖቶች ዘርፋችሁ ሄዳችሁ፤ ታዲያ እኔ ምን ተረፈኝ?” አላቸው።


የዳን ሰዎችም ያመልኩት ዘንድ ያን ጣዖት በዚያ አኖሩ፤ ከሙሴ ልጅ ከጌርሾም የተወለደው ዮናታንም ለዳን ነገድ ካህን ሆኖ ማገልገል ጀመረ። የእርሱም ዘሮች ሕዝቡ ተማርከው እስከ ተሰደዱበት ጊዜ ድረስ ማገልገላቸውን ቀጠሉ።


ጌዴዎንም ከዚያ ወርቅ ጣዖት ሠርቶ በትውልድ ከተማው በዖፍራ አኖረው፤ እስራኤላውያንም በሙሉ ከእግዚአብሔር ተለይተው ያንን ማምለክ ጀመሩ፤ ለጌዴዎንና ለቤተሰቡ ሁሉ መሰናከያ ወጥመድ ሆነ።


ከዚህ በኋላ የቤተሰቡን ጣዖት ወስዳ በአልጋ ላይ አጋደመችው፤ ከፍየል ጠጒር የተሠራ ትራስም በራስጌው አኑራ በልብስ ሸፈነችው።


የአቤሜሌክ ልጅ አብያታር አምልጦ በቀዒላ ከዳዊት ጋር በተባበረ ጊዜ ወደዚያ የመጣው ኤፉዱን እንደ ያዘ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos