Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 17:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በዚያን ጊዜ በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱም ሰው ለራሱ ደስ ያለውን ነገር ሁሉ እንደ ፈለገ ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱም ሰው መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሰውም ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን ያደ​ርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፥ ሰውም ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 17:6
13 Referencias Cruzadas  

በእስራኤል ንጉሥ መንገሥ ከመጀመሩ በፊት በኤዶም ምድር የነገሡት ነገሥታት የሚከተሉት ናቸው፤


እነርሱ፦ “በመናገራችን የፈለግነውን እናገኛለን፤ እንደ ፈቀድን እንናገራለን፤ ሊከለክለን የሚችል ማን ነው?” ይላሉ።


ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ሁልጊዜ ትክክል የሆኑ ይመስላቸዋል፤ ጠቢባን ግን መልካም ምክርን ይቀበላሉ።


አንተ “ትክክለኛ መንገድ ነው” ብለህ የምታስበው ወደ ሞት ይመራህ ይሆናል።


ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል የሆነ ሊመስለው ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ዓላማውን ይመዝናል።


ወጣት ሆይ! ወጣትነት እጅግ ግሩም ስለ ሆነ በወጣትነትህ ዘመን ደስ ይበልህ፤ በልብህም ሐሤት አድርግ፤ ዐይንህ የሚያየውንና ልብህ የሚመኘውን ሁሉ ፈጽም፤ ሆኖም ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።


“ያ ሰዓት በሚደርስበት ጊዜ እስከ አሁን እንደ ፈለጋችሁ በምትፈጽሙት ዐይነት አታደርጉም፤ እነሆ እስከ አሁን የመሰላችሁን ታደርጉ ነበር፤


የእስራኤል ነገዶችና የሕዝቡ መሪዎች በተሰበሰቡ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ነገሠ።”


በዚያም ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ በእስራኤል ነገዶች መካከል የራሳቸው የሆነ የርስት ድርሻ ገና ያላገኙ ስለ ነበሩ የዳን ነገድ ተወላጆች የሚሰፍሩበትን ርስት ለማግኘት በመፈለግ ላይ ነበሩ።


በእስራኤል ገና ንጉሥ ባልነበረበት ጊዜ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ራቅ ብሎ በሚገኝ ስፍራ የሚኖር አንድ ሌዋዊ ነበረ፤ ይህ ሰው በይሁዳ ግዛት ከምትገኘው ከቤተልሔም አንዲት ልጃገረድ ቊባት ወስዶ ነበር፤


በዚያም ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱም ሰው ለራሱ ደስ ያለውን ነገር ሁሉ እንደ ፈለገ ያደርግ ነበር።


እነርሱም፦ አቤቱ፥ የእስራኤል አምላክ ሆይ! ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ መታጣቱ፥ ስለምን ይህ በእስራኤል ላይ ሆነ? አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos