መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ያገልግሉህ፤ በወንድሞችህ ሁሉ ላይ አለቃ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚመርቁህም የተመረቁ ይሁኑ።”
ዘኍል 24:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤዶምን አሸንፎ የራሱ ያደርጋታል፤ ጠላቱ ሴርም የእርሱ ትሆናለች፤ እስራኤል ድል አድራጊ እንደ ሆነ ይኖራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤዶም ይሸነፋል፤ ጠላቱ ሴይርም ድል ይሆናል፤ እስራኤል ግን እየበረታ ይሄዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፥ ጠላቱ ሴይር ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኃይል ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፤ ጠላቱ ኤሳው ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኀይል ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፥ ጠላቱ ሴይር ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኃይል ያደርጋል። |
መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ያገልግሉህ፤ በወንድሞችህ ሁሉ ላይ አለቃ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚመርቁህም የተመረቁ ይሁኑ።”
በመላው ኤዶም ብዙ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የእርሱ ተገዢዎች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።
ከኤዶም ቦጽራ ቀይ መጐናጸፊያ ተጐናጽፎ የሚመጣው ይህ ማነው? በታላቅ ኀይሉ አስደናቂ ልብስ ለብሶ የሚራመደው ይህ ማነው? “ፍርድን የምሰጥ የማዳን ኀይል ያለኝ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ፈራርሶ እንደ ወደቀ ቤት የነበረውን የዳዊትን ሥርወ መንግሥት መልሼ የማቋቊምበት ጊዜ ይመጣል፤ ቅጽሩን እጠግናለሁ፤ ፍርስራሹንም አድሳለሁ፤ በቀድሞ ዘመን እንደ ነበረውም አድርጌ እሠራዋለሁ፤