Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 24:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ኤዶ​ም​ያ​ስም ርስቱ ይሆ​ናል፤ ጠላቱ ኤሳው ደግሞ ርስቱ ይሆ​ናል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በኀ​ይል ያደ​ር​ጋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኤዶም ይሸነፋል፤ ጠላቱ ሴይርም ድል ይሆናል፤ እስራኤል ግን እየበረታ ይሄዳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፥ ጠላቱ ሴይር ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኃይል ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ኤዶምን አሸንፎ የራሱ ያደርጋታል፤ ጠላቱ ሴርም የእርሱ ትሆናለች፤ እስራኤል ድል አድራጊ እንደ ሆነ ይኖራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፥ ጠላቱ ሴይር ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኃይል ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 24:18
15 Referencias Cruzadas  

ይኸ​ውም የቀሩ ሰዎ​ች​ንና ስሜም የተ​ጠ​ራ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ይፈ​ልጉ ዘንድ ነው” ይላል ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


መላ​ዋን ኤዶ​ም​ያ​ስን ይጠ​ብቁ ዘንድ በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፤ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ዳዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሚ​ሄ​ድ​በት ቦታ ሁሉ ጠበ​ቀው።


አሕ​ዛብ ይገ​ዙ​ልህ፤ አለ​ቆ​ችም ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ጌታ ሁን፤ የአ​ባ​ት​ህም ልጆች ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ የሚ​ረ​ግ​ምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚ​ባ​ር​ክ​ህም ቡሩክ ይሁን።”


ከኤ​ዶ​ም​ያስ፥ ከባ​ሶራ የሚ​መጣ፥ ልብ​ሱም የቀላ፥ የሚ​መካ ኀይ​ለኛ፥ አለ​ባ​በ​ሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የም​ከ​ራ​ከር፥ ስለ ማዳ​ንም የም​ፈ​ርድ እኔ ነኝ።


ሰይፌ በሰ​ማይ ሆና ሰከ​ረች፤ እነሆ፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስና በሚ​ጠ​ፉት ሕዝብ ላይ ለፍ​ርድ ትወ​ር​ዳ​ለች።


አም​ላኬ ሆይ፥ ልመ​ና​ዬን ስማኝ፥ ጸሎ​ቴ​ንም አድ​ም​ጠኝ።


ያዕ​ቆ​ብም ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም ሀገር በፊቱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤


በሰ​ይ​ፍ​ህም ትኖ​ራ​ለህ፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ትገ​ዛ​ለህ፤ ነገር ግን ቀን​በ​ሩን ከአ​ን​ገ​ትህ ልት​ጥል ብት​ወ​ድድ ከእ​ርሱ ጋር ተስ​ማማ።”


የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ “በእኔ በኩል አታ​ል​ፍም፤ ይህ ካል​ሆነ ግን እን​ዋ​ጋ​ለን፤ በጦ​ርም እቀ​በ​ልህ ዘንድ እወ​ጣ​ለሁ” አለው።


ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀያል ሰው ይወ​ጣል፤ ከከ​ተ​ማ​ውም የቀ​ሩ​ትን ያጠ​ፋል።”


“በዚያ ቀን የወ​ደ​ቀ​ች​ውን የዳ​ዊ​ትን ቤት አነ​ሣ​ለሁ፤ የተ​ና​ደ​ው​ንም ቅጥ​ር​ዋን እጠ​ግ​ና​ለሁ፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም አድ​ሳ​ለሁ፤ እንደ ቀደ​መ​ውም ዘመን እሠ​ራ​ታ​ለሁ፤


እነሆ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ታናሽ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ አንተ እጅግ ተን​ቀ​ሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኤዶ​ማ​ዊው አዴ​ርን ከረ​ም​ማ​ቴር ወገን የኤ​ል​ያ​ዳሔ ልጅ ኤስ​ሮ​ምን የሲባ ንጉሥ ጌታ​ውን አድ​ረ​ዓ​ዛ​ርን ጠላት አድ​ርጎ በሰ​ሎ​ሞን ላይ አስ​ነሣ። ሰዎ​ችም ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ። የዓ​መ​ፁም አበ​ጋዝ እርሱ ነበር። ደማ​ስ​ቆ​ንም እጅ አደ​ረ​ጋት። በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠላት ሆነ። ኤዶ​ማ​ዊው አዴ​ርም ከኤ​ዶ​ም​ያስ ነገ​ሥ​ታት ዘር ነበር።


ዳዊ​ትም ኤዶ​ም​ያ​ስን ባጠፋ ጊዜ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ኢዮ​አብ ተወ​ግ​ተው የሞ​ቱ​ትን ሊቀ​ብር በወጣ ጊዜ፥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንም ወንድ ሁሉ በገ​ደለ ጊዜ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios