ኢሳይያስ 63:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ከኤዶም ቦጽራ ቀይ መጐናጸፊያ ተጐናጽፎ የሚመጣው ይህ ማነው? በታላቅ ኀይሉ አስደናቂ ልብስ ለብሶ የሚራመደው ይህ ማነው? “ፍርድን የምሰጥ የማዳን ኀይል ያለኝ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ይህ ከኤዶም፣ ቀይ የተነከረ መጐናጸፊያ ለብሶ ከባሶራ የሚመጣ ማን ነው? ይህ ክብርን የተጐናጸፈ፣ በኀይሉ ታላቅነት እየተራመደ የሚመጣውስ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር፣ ለማዳንም ኀይል ያለኝ እኔው ነኝ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጉልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ከኤዶምያስ፥ ከባሶራ የሚመጣ፥ ልብሱም የቀላ፥ የሚመካ ኀይለኛ፥ አለባበሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የምከራከር፥ ስለ ማዳንም የምፈርድ እኔ ነኝ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጕልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው? በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ። Ver Capítulo |