Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አሞጽ 9:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚህም ዐይነት ከኤዶም ምድር የተረፉትንና ሌሎችንም በስሜ የተጠሩትን ሕዝብ ሁሉ ይወርሳሉ፤” ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ስለዚህ የኤዶምን ትሩፍ፣ በስሜ የተጠሩትንም ሕዝቦች ሁሉ ይወርሳሉ፤” ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ይኸውም የኤዶምያስን ትሩፍ፥ ስሜም የተጠራባቸውን አሕዛብን ሁሉ እንዲወርሱ ነው፥” ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ይኸ​ውም የቀሩ ሰዎ​ች​ንና ስሜም የተ​ጠ​ራ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ይፈ​ልጉ ዘንድ ነው” ይላል ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ይኸውም የኤዶምያስን ቅሬታ፥ ስሜም የተጠራባቸውን አሕዛብን ሁሉ ይወርሱ ዘንድ ነው፥ ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 9:12
17 Referencias Cruzadas  

መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ያገልግሉህ፤ በወንድሞችህ ሁሉ ላይ አለቃ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚመርቁህም የተመረቁ ይሁኑ።”


ይስሐቅም “ቀደም ብዬ እርሱን የአንተ ጌታ አድርጌዋለሁ፤ ወንድሞቹ ሁሉ የእርሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጌአለሁ፤ እህልና የወይን ጠጅ እንዲበዛለት አድርጌአለሁ፤ ልጄ ሆይ! እንግዲህ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?” አለው።


ሞአብ መታጠቢያዬ ነው፤ ኤዶም የእኔ መሆኑን ለማረጋገጥ ጫማዬን አኖርበታለሁ፤ በፍልስጥኤማውያንም ላይ።”


ሁለቱም ተባብረው በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤማውያን ላይ ይነሣሉ፤ በስተ ምሥራቅ የሚኖሩ ሕዝቦችንም ሀብት ይዘርፋሉ፤ የኤዶምንና የሞአብን ሕዝብ ድል ይነሣሉ፤ የዐሞንም ሕዝብ ለእነርሱ ታዛዦች ይሆናሉ።


እነርሱ በስሜ የተጠሩና ለክብሬ የፈጠርኳቸው በእጄም የአበጀኋቸውና የሠራኋቸው ሕዝቤ ናቸው።”


እኛ በአንተ እንዳልተገዙና በስምህ እንዳልተጠሩ ወገኖች ከሆንን ብዙ ጊዜአችን ነው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔን ላልጠየቁኝ ተገለጥኩላቸው፤ ላልፈለጉኝም ተገኘሁላቸው፤ ስሜንም ላልጠራ ሕዝብ ‘እነሆ፥ እዚህ አለሁ፥ እነሆ፥ እዚህ አለሁ’ አልኳቸው።


ለምን ግራ እንደ ተጋባ ሰውና ሌላውን መርዳት እንደማይችል ኀይለኛ ወታደር ትሆናለህ? እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን በመካከላችን ነህ፤ በስምህም እንጠራለን፤ እባክህ አትተወን።’ ”


የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እኔ በስምህ ተጠርቼአለሁ፤ ቃልህ ወደ እኔ በመጣ ጊዜ በሙሉ ተቀብዬዋለሁ፤ ልቤንም በደስታና በሐሴት ሞላው።


የእናንተንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ለይሁዳ ሕዝብ ተላልፈው እንዲሸጡ አደርጋለሁ፤ እነርሱም ሩቅ ላሉት ለሳባውያን ይሸጡአቸዋል፤ ይህንንም የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ኤዶማውያን የተባሉ የዔሳው ተወላጆች “ከተሞቻችን ፈራርሰዋል፤ ነገር ግን መልሰን እንሠራቸዋለን” ቢሉ የሠራዊት አምላክ ደግሞ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ ይሠራሉ፤ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ ሕዝቡም ሁሉ አገሪቱን ‘የክፋት ምድር’ ኗሪዎቹንም ‘እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተቈጣው ሕዝብ’ ብለው ይጠሯቸዋል።”


ይህንንም የማደርገው የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ እኔን እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ ነው፤


ከጥንት ጀምሮ ይህን ሁሉ ያስታወቅኹ እኔ እግዚአብሔር እንዲህ እላለሁ፤’


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos