ዘኍል 20:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሮን ለእስራኤላውያን ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር አይገባም፤ እናንተ ሁለታችሁ በመሪባ ውሃ ዘንድ በትእዛዜ ላይ ስላመፃችሁ አሮን ይሞታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሮን ወደ ወገኖቹ ይሰበሰባል፤ ሁለታችሁም በመሪባ ውሃ በትእዛዜ ላይ ዐምፃችኋልና ለእስራኤላውያን ወደምሰጣት ምድር አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሮን ወደ ወገኑ ይከማች፤ በመሪባ ውኃ ዘንድ በትእዛዜ ላይ ስላመፃችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሮን ወደ ወገኑ ይጨመር፤ በክርክር ውኃ ዘንድ ስለ አሳዘናችሁኝ ለእስራኤል ልጆች ወደ ሰጠኋት ምድር አትገቡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮን ወደ ወገኑ ይከማች፤ በመሪባ ውኃ ዘንድ በቃሌ ላይ ስለ ዓመፃችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባም። |
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “እኔ በሞት ወደ ወገኖቼ የምሄድበት ጊዜ ደርሶአል፤ ስለዚህ በሒታዊው በዔፍሮን እርሻ ላይ ባለው ዋሻ ውስጥ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤
አንተ በሕይወት እስካለህ ድረስ በኢየሩሳሌም ላይ ቅጣት አላመጣም፤ አንተ በሰላም እንድትሞት አደርጋለሁ።’ ” ሰዎቹም ይህን መልእክት ይዘው ወደ ንጉሥ ኢዮስያስ ተመለሱ።
እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።
ከግብጽ አውጥታችሁ ምንም ነገር ወደማይበቅልበት ወደዚህ አስከፊ ምድር ለምን አመጣችሁን? በዚህ ስፍራ እህል፥ በለስ፥ ወይንና ሮማን አይገኝም፤ ሌላው ቀርቶ የሚጠጣ ውሃ እንኳ የለም!”
በሚሸከሙአቸው ነገሮችና በሚሠሩአቸው ሥራዎች የጌርሾንን ልጆች አገልግሎት አሮንና ልጆቹ ይቈጣጠሩአቸዋል፤ መሸከም ያለባቸውንም ነገሮች ሁሉ ትመድብላቸዋለህ።
ስለ ሌዊም ነገድ እንዲህ አለ፦ “ጌታ ሆይ! በቱሚምና በዑሪም አማካይነት በማሳና በመሪባ ውሃ ዘንድ ተከራክረህ ለፈተንካቸው ለአገልጋዮችህ ለሌዋውያን ፈቃድህን ግለጥ።
እንዲህ አለቻቸው፦ “የሀገሪቱ ኗሪዎች በሙሉ በፍርሃት ተውጠው ልባቸው ቀለጠ፤ በሁላችንም ላይ ፍርሀት ስላደረብን እግዚአብሔር ምድሪቱን ለእናንተ እንደ ሰጠ ዐውቃለሁ፤