ዘኍል 13:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሰዎቹ ወደ ሰሜን ሄዱ፤ በአገሪቱም ከሚገኘው ከጺን ምድረ በዳ ጀምረው ለሐማት መተላለፊያ ቅርብ እስከሆነው ረሖብ ድረስ አጠኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ወጥተው ከጺን ምድረ በዳ አንሥቶ በሌቦ ሐማት በኩል እስከ ረአብ ድረስ ዘልቀው ምድሪቱን አጠኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወጡም ምድሪቱንም ከጺን ምድረ በዳ ለሌብ ሐማት ቅርብ እስከሆነችው እስከ ረዓብ ድረስ ሰለሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወጡም፤ ምድሪቱንም ከጺን ምድረ በዳ በኤማት ዳር እስካለችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወጡም ምድሪቱንም ከጺን ምድረ በዳ በሐማት ዳር እስካለችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ። |
“የሐማትና የአርፋድ ከተማ ነዋሪዎች የደማስቆን የጥፋት ወሬ ስለ ሰሙ ግራ ተጋቡ፤ ወደ ላይና ወደ ታች እንደሚናወጥ ባሕር የእነርሱም ልብ ተሸበረ።
ሴዴቅያስም ወደ ንጉሥ ናቡከደነፆር ተወሰደ፤ ናቡከደነፆር በዚያን ጊዜ በሐማት ግዛት ሪብላ ተብላ በምትጠራ ከተማ ውስጥ ነበር፤ እዚያም ናቡከደነፆር በሴዴቅያስ ላይ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈበት።
በደማስቆና በሐማት መካከል ወደሚገኙት ወደ ቤሮታና ሲብራይም ከተሞች፥ በሐውራን ጠረፍ ወደምትገኘው ወደ ቲኮን ከተማ እስከ ምሥራቅ ይዘልቃል።
እስቲ ወደ ካልኔ ከተማ ሄዳችሁ ተመልከቱ፤ ከዚያም አልፋችሁ “ሐማት” ተብላ ወደምትጠራው ታላቂቱ ከተማና የፍልስጥኤማውያን ከተማ ወደሆነችው ወደ ጋት ውረዱ፤ እናንተ ከእነርሱ ትበልጣላችሁን? ግዛታችሁስ ከእነርሱ ግዛት ይበልጣልን?
ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ በትእዛዜ ላይ ዐምፃችሁ ነበር፤ መላው ማኅበር በመሪባ ውሃ ዘንድ ሳሉ በእኔ ላይ በዐመፁ ጊዜ የተቀደሰውን ኀይሌን በእነርሱ ፊት መግለጥ እምቢ ብላችኋል፤” (መሪባ በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ የሚገኝ ምንጭ ነው።)
እናንተ ሁለታችሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ለእኔ ታማኞች ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ከተማ አጠገብ በምትገኘው በመሪባ ውሃ ምንጮች አጠገብ በነበራችሁበት ጊዜ በእስራኤል ሕዝብ ፊት እንድከበር አላደረጋችሁም።
የጌባላውያን ምድርና ከምሥራቅ በአርሞንኤም ተራራ ደቡብ ከሚገኘው ከባዓልጋድ ተነሥቶ እስከ ሐማት መተላለፊያ ያለው መላው ሊባኖስ ገና አልተያዘም።
የላይሽ ሕዝብ ከማንም ጋር ግንኙነት ስላልነበራቸውና ከሲዶንም ርቀው ይኖሩ ስለ ነበረ የሚያድናቸው አልተገኘም። ከተማዋ በቤትረሖብ አጠገብ በሚገኝ ሸለቆ ውስጥ ነበረች፤ የዳን ሰዎችም ከተማዋን እንደገና ሠርተው ኖሩባት።