በዳዊት ዘመነ መንግሥት ሦስት ዓመት ሙሉ ጽኑ ራብ ነበር፤ ዳዊትም ስለዚህ ጉዳይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጠየቀ ጊዜ እግዚአብሔር “ሳኦልና ቤተሰቡ ግድያ በመፈጸም በደል ሠርተዋል፤ ሳኦልም የገባዖንን ሰዎች ፈጅቶአል” ሲል መለሰለት።
ሚክያስ 6:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ እርሱ ከተማይቱን እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በከተማይቱ የተሰበሰባችሁ ሰዎች አድምጡ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፤ ስሙ! እግዚአብሔር ከተማዪቱን እንዲህ እያለ ይጣራል፤ “በትሩን አስቡ፤ ያዘጋጀውም ማን እንደ ሆነ አስታውሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፤ ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፤ ወገን ሆይ፥ ያዘጋጀው ማን እንደሆነ ስሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፥ ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፥ የመቅሠፍትን በትር፥ እርሱንም ያዘጋጀ ማን እንደ ሆነ ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፥ ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፥ የመቅሠፍትን በትር፥ እርሱንም ያዘጋጀ ማን እንደ ሆነ ስሙ። |
በዳዊት ዘመነ መንግሥት ሦስት ዓመት ሙሉ ጽኑ ራብ ነበር፤ ዳዊትም ስለዚህ ጉዳይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጠየቀ ጊዜ እግዚአብሔር “ሳኦልና ቤተሰቡ ግድያ በመፈጸም በደል ሠርተዋል፤ ሳኦልም የገባዖንን ሰዎች ፈጅቶአል” ሲል መለሰለት።
አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።
የተመሸገችው ከተማ ፈራርሳለች፤ ባዶዋን ቀርታ ጭው ያለ ምድረ በዳ መስላለች፤ የከብቶች መሰማሪያ ስለ ሆነች በዚያ ጥጆች የዛፍ ቅርንጫፎችን እየበሉ ያርፋሉ።
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ኀይልና ግርማ ከሩቅ ይታያል፤ ነበልባልና ጢስ የቊጣው ምልክቶች ናቸው፤ በሚናገርበትም ጊዜ ቃሉ እንደ እሳት ይነዳል።
በከተማ የሚሰማውን ሁካታ አድምጡ! ከቤተ መቅደስም ድምፅ ስሙ፤ ይህም እኔ እግዚአብሔር ለጠላቶቼ ተገቢ ዋጋቸውን በምሰጥበት ጊዜ የሚሰማ ድምፅ ነው።”
“ሕዝቅያስ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን የሞሬሼቱ ነቢይ ሚክያስ የሠራዊት አምላክ የተናገረውን የትንቢት ቃል ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ዐውጆ ነበር፦ ‘ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ ቤተ መቅደሱም የተሠራበት ኰረብታ ዳዋ ይበቅልበታል።’
ባለመታዘዛችሁ የምትቀጥሉበት ከሆነ በሴሎ ያደረግኹትን ሁሉ በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ ደግሜ አደርጋለሁ፤ የዓለም ሕዝብ ሁሉ የዚህችን የከተማ ስም እንደ መራገሚያ ይቈጥራል።”
ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር የሰጠሁትን ሥራ ሳይፈጽም እንዴት ማረፍ ይችላል? እኔ በአስቀሎናና በጠረፎችዋ በሚኖሩ ሕዝብ ላይ አደጋ እንዲጥል አዝዤዋለሁ።”
ከቶ አልራራላችሁም፤ ምሕረትም አላደርግላችሁም፤ በርኲሰት ላይ እስካላችሁ ድረስ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ የምቀጣችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
ሰማርያ በእኔ ላይ በማመፅዋ በሠራችው በደል ተጠያቂ ትሆናለች፤ ሕዝብዋም በጦርነት ይሞታሉ፤ ሕፃናት በምድር ላይ ይፈጠፈጣሉ፤ እርጉዞችም ሆዳቸው ይሰነጠቃል።”
ጥበብ ያላቸው እነዚህን ነገሮች ይረዳሉ፤ አስተዋዮችም ያውቋቸዋል፤ የእግዚአብሔር መንገድ ትክክል ነው፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ኃጢአተኞች ግን ይሰናከሉበታል።
የእስራኤል ሕዝብ ርዳታቸውን ፈልጎ ወደ መሪዎቹ ይመጣል፤ እነርሱ ግን በጽዮን ተዝናንተው ስለሚቀመጡና በሰማርያ ተራራ ላይ ያለ ሥጋት ስለሚኖሩ ለእነዚህ ታዋቂ መሪዎች ወዮላቸው!
ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ ቤተ መቅደሱም የተሠራበት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ይሆናል።
እግዚአብሔር መልካም የሆነውንና ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል፤ ይኸውም ፍትሕን እንድትጠብቅ፥ ደግነትን እንድትወድ፥ ከአምላክህ ጋር በትሕትና እንድትመላለስ ነው።