Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሶፎንያስ 3:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ማንንም አታዳምጥም፤ ተግሣጽም አትቀበልም፤ በእግዚአብሔር አትተማመንም፤ ወደ አምላክዋም አትቀርብም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እርሷ ለማንም አትታዘዝም፤ የማንንም ዕርምት አትቀበልም፤ በእግዚአብሔር አትታመንም፤ ወደ አምላኳም አትቀርብም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ማንንም አታዳምጥም፥ እርምት አትቀበልም፥ በጌታ አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ድምፅን አልሰማችም፥ ተግሣጽንም አልተቀበለችም፣ በእግዚአብሔርም አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ድምፅን አልሰማችም፥ ተግሣጽንም አልተቀበለችም፥ በእግዚአብሔርም አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም።

Ver Capítulo Copiar




ሶፎንያስ 3:2
30 Referencias Cruzadas  

በብልጽግና በምትኖሩበት ጊዜ እግዚአብሔር ተናገራችሁ፤ እናንተ ግን ማዳመጥ እምቢ አላችሁ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ የምታደርጉት ይህንኑ ነው። እግዚአብሔርንም መታዘዝ እምቢ አላችሁ።


እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።


እነርሱ እኔን ትተው ሄደዋል፤ ዘወትር በመደጋገም ባስተምራቸውም አልሰሙኝም፤ ተግሣጼንም አልተቀበሉም፤


ከቶ የምትታረሙ ስላልሆናችሁ፥ እኔ እናንተን መቅጣቴ ከንቱ ነው፤ እንደ ተቈጣ አንበሳ ሆናችሁ ነቢያቶቻችሁን በሰይፍ ገደላችሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል! “የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ፥ እናንተ ስሜን መጥራት ትታችኋል፤ ልታገለግሉኝም አልፈለጋችሁም።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።


እንዲህም ትላለህ፦ “የማልማረውና የሰውን ተግሣጽ የማልቀበለው ከቶ ለምንድን ነው!


ይህም የሆነው በእርሱ ስላላመኑና እንደሚያድናቸውም ስላልተማመኑበት ነው።


ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረቤ መልካም ነው፤ የአንተን ሥራ ሁሉ ለማብሠር እንድችል አንተን ጌታ አምላኬን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ።


ስሕተትህን መታረም ትጠላለህ፤ ቃሎቼንም ትንቃለህ።


ክፉዎች ስለ እግዚአብሔር ግድ የላቸውም በትዕቢታቸውም እግዚአብሔር የለም ብለው ያስባሉ።


“ነገር ግን እነርሱ በአንተ ላይ ዐምፀው ለቃልህ አንታዘዝም አሉ፤ ሕግህንም ላለመስማት ፊታቸውን መለሱ፤ በማስጠንቀቅ ወደ አንተ እንዲመለሱ ያስተማሩአቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ በየጊዜውም በአንተ ላይ ክፉ የስድብ ቃል ተናገሩ፤


ስለዚህ ከክፉ ኅሊና እንድንነጻ ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፥ ቅን ልብና እውነተኛ እምነት ይዘን ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።


ኢየሩሳሌም ሆይ! ሴሰኛነትሽ አርክሶሻል፤ እኔ እንኳ ላነጻሽ ብፈቅድ አንቺ ከርኲሰትሽ አልነጻሽም። የቊጣዬ ኀይል እስከሚገለጥብሽ ድረስ ዳግመኛ ንጹሕ አትሆኚም።


ስለዚህም እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አደርስባችኋለሁ ብዬ የተናገርኩትን ጥፋት ሁሉ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሆናችሁት ሁሉ ላይ አመጣባችኋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ስነግራችሁ ባለማዳመጣችሁና ስጠራችሁም መልስ ባለመስጠታችሁ ነው።”


ብዙ ፈረሶች፥ ሠረገሎችና ወታደሮች ባሉት ብርቱ በሆነው በግብጽ ሠራዊት ተማምነው ርዳታ ለማግኘት ወደ ግብጽ ለሚወርዱ ወዮላቸው! ነገር ግን የእስራኤልን ቅዱስ ርዳታ አይለምኑም፤ መመሪያውንም አይቀበሉም።


በዐመፅ ላይ ዐመፅ ጨምራችሁ እንደገና መቀጣት የምትፈልጉት ለምንድን ነው? ራሳችሁ ለሕመም፥ ልባችሁም ሁሉ ለድካም የተጋለጠ ሆኖአል።


እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ሞኞች ግን ጥበብና ሥነ ሥርዓትን ይንቃሉ።


ቅዱስ መጽሐፍ በሙሉ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ ነው፤ እርሱ እውነትን ለማስተማር፥ የተሳሳቱትን ለመገሠጽ፥ ስሕተትን ለማረምና ለትክክለኛ ኑሮ የሚበጀውን መመሪያ ለመስጠት ይጠቅማል።


ዕድል ፈንታችሁም ይህ እንደሚሆን እግዚአብሔር ተናግሮአል። እርሱን ረስታችሁ በሐሰተኞች አማልክት ስለ ታመናችሁ በእናንተ ላይ ይህን ለማድረግ ወስኖአል።


“የሰው ልጅ ሆይ! ምድራቸው ስለ ረከሰች በቊጣዬ ዝናብ እንዳይዘንብ በማድረግ ልቀጣት የተዘጋጀሁ መሆኑን ለእስራኤላውያን ንገራቸው፤


እርሱ ከምሥራቅ ሶርያውያንን፥ ከምዕራብ ፍልስጥኤማውያንን ልኮ እስራኤልን እንዲወሩ አደረገ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ቊጣው አልበረደም፤ ስለዚህ እጁ እነርሱን ለመቅጣት እንደ ተቃጣ ነው።


ከእኔ የራቁትን፥ እኔን መከተል የተዉትንና ወደ እኔም መጥተው እኔ እንድመራቸው ያልጠየቁኝን አጠፋለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios