ሉቃስ 7:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና “አይዞሽ፥ አታልቅሺ!” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፣ “አይዞሽ፤ አታልቅሺ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፦ “አታልቅሽ፤” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችንም በአያት ጊዜ አዘነላትና፥ “አታልቅሺ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታም ባያት ጊዜ አዘነላትና፦ አታልቅሽ አላት። |
በችግራቸው ጊዜ ሁሉ ያዳናቸው በመልእክተኛ ወይም በመልአክ አማካይነት ሳይሆን እርሱ በመካከላቸው በመገኘት ነው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ታደጋቸው፤ እርሱም በቀድሞ ዘመናት ሁሉ አንሥቶ ልጁን እንደሚሸከም ሰው ተንከባከባቸው።
“እስራኤል ሆይ! እናንተ የተወደዳችሁ ልጆቼ ናችሁ፤ ከሁሉ አስበልጬ የምወዳችሁ አይደለምን? ምሕረት አደርግላችሁ ዘንድ ወደ እኔ ላቀርባችሁ እፈቅዳለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ከዚህ በኋላ ጌታ፥ ሌሎች ሰባ ሁለት ሰዎችን መረጠ፤ እርሱ ሊሄድበት ወደአሰበውም ከተማና ቦታ ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው።
አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም ባበቃ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ! ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው፥ አንተም እኛን መጸለይ አስተምረን!” አለው።
ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ “እናንተ ፈሪሳውያን የብርጭቆውንና የሳሕኑን ውጪውን አጥርታችሁ ታጥባላችሁ፤ በውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶባችኋል።
ጌታ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ታዲያ ቤተሰቦቹን በደንብ እንዲያስተዳድርለትና ለአገልጋዮቹም ምግባቸውን በተመደበው ጊዜ እንዲሰጣቸው ጌታው የሚሾመው ታማኝና ብልኅ መጋቢ ማን ነው?
ጌታ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተስ እያንዳንዱ በሰንበት ቀን በሬውን ከተዘጋበት አውጥቶ፥ ወይም አህያውን ከታሰረበት ፈቶ ውሃ ወደሚያጠጣበት ቦታ ይወስደው የለምን?
ጌታ ኢየሱስም “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያኽል እምነት ቢኖራችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ በባሕር ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዝላችኋል” አላቸው።
ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታ ኢየሱስን እንዲህ አለው፦ “ጌታ ሆይ! እነሆ፥ ካለኝ ሀብት ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ በማታለል ከሰው ላይ የወሰድኩትም ገንዘብ ቢኖር፥ አራት እጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ።”
በዚህ ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ዞር ብሎ ጴጥሮስን አየው፤ ጴጥሮስም “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” በማለት ጌታ ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አስታወሰ።
ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ በር አጠገብ ሲደርስ እነሆ፥ ሰዎች ሬሳ ተሸክመው ከከተማይቱ ይወጡ ነበር፤ የሞተው ሰው ለእናቱ አንድ ነበር፤ እናቱም ባልዋ የሞተባት መበለት ነበረች፤ ከከተማይቱም ብዙ ሰዎች ተከትለዋት ነበር።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደፊት ራመድ ብሎ ቃሬዛውን ነካ፤ ቃሬዛውንም የተሸከሙት ሰዎች ቆሙ፤ ኢየሱስም “አንተ ወጣት ተነሥ እልሃለሁ!” አለ።
በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ስለ ልጅትዋ ያለቅሱ! ዋይ ዋይም ይሉ ነበር። ኢየሱስ ግን “አታልቅሱ፤ ልጅትዋ አንቀላፍታለች እንጂ አልሞተችም፤” አላቸው።
ኢየሱስ፥ “አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሺአለሽ፤ ማንንስ ትፈልጊአለሽ?” አላት። እርስዋም አትክልተኛው መስሎአት፥ “ጌታ ሆይ! አንተ ወስደኸው እንደ ሆነ የት እንዳኖርከው እባክህ ንገረኝ፤ እኔ እወስደዋለሁ” አለችው።
ስለዚህ በሁሉም ነገር እንደ ወንድሞቹ መሆን ነበረበት፤ በዚህ ዐይነት የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ ብሎ እግዚአብሔርን ለማገልገል ታማኝና መሐሪ የካህናት አለቃ ሆነ።