ይሁዳ 1:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንዶችን ከእሳት አውጥታችሁ አድኑአቸው፤ ለሌሎች በፍርሃት ራሩላቸው፤ ሆኖም በኃጢአት የረከሰውን ሰውነታቸውን የነካውን ልብስ እንኳ ሳይቀር ጥሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንዶችን ከእሳት ነጥቃችሁ አድኗቸው፤ ለሌሎች ደግሞ በርኩስ ሥጋ የተበከለውን ልብሳቸውን እንኳ እየጠላችሁ በፍርሀት ምሕረት አሳዩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዳንዶቹን ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑአቸው፤ አንዳንዶቹን በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ምሕረት አድርጉላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ። |
እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ደመሰስኩ ከእናንተም ብዙዎችን ደመሰስኩ፤ እናንተም የተረፋችሁት በእሳት ከተቀጣጠለ በኋላ ተነጥቆ እንደ ወጣ እንጨት ነው፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
ይህንንም ማድረጌ የሥጋ ዘመዶቼ የሆኑትን አይሁድ ለማስቀናት ነው፤ በዚህም ሁኔታ ምናልባት ከእነርሱ አንዳንዶቹን ለማዳን እችል ይሆናል በማለት ነው።
ሥራው በእሳት ተቃጥሎ የተደመሰሰበት ግንበኛ ግን ዋጋው ይቀርበታል፤ ይሁን እንጂ እርሱ ራሱ፥ በእሳት ውስጥ አልፎ ሳይቃጠል እንደሚቀር ሰው ይድናል።
ጌታን መፍራት ምን መሆኑን ስለምናውቅ ሰዎችን እናስረዳለን፤ እኛ ምን መሆናችንንም እግዚአብሔር ያውቃል፤ እናንተም በልቡናችሁ ምን መሆናችንን እንደምታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ።
በዚህ መልእክት ያስተላለፍንላችሁን ምክር የማይቀበል ሰው ቢኖር እንዲህ ያለውን ሰው ልብ በሉት፤ እንዲያፍርም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አታድርጉ።
ሀብታም ለመሆን በእሳት የተፈተነውን ወርቅ ከእኔ እንድትገዛ፥ የራቊትነትህን ኀፍረት ለመሸፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ፥ ለማየትም እንድችል የዐይን መድኃኒት ገዝተህ እንድትቀባ እመክርሃለሁ።
ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ እነርሱ ነጭ ልብስ መልበስ የሚገባቸው ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።